የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለዋናው መስሪያ ቤት ሰራተኞች የዓይን መነፅር ሥራ አገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 04, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ

የጨረታ ቁጥር RE-LP/OT/13/S/G/2018

1. የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለዋናው መ/ቤት ሰራተኞች የዓይን መነፅር ሥራ አገልግሎት ግዥ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በቁ ተጫራቾች ህጋዊ ለ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታክስ ክሊራንስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ሠርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት እና የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ የሚመለከተው የመንግስት አካል ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች አገልግሎት ሰጪ ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡

3. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ለኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ሂሳብ ቁጥር 1000000888862 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00 ፣ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-11፡00 ቍጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ

ግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ

ሜክሲኮ አካባቢ ከሚገኘው ስልሳም ጨስስቅ ህንፃ ፊት ለፌት፣

ፈሊፒስ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220

ስልክ ቁጥር 011 5 51 62 71/50 04 17 አዲስ አበባ፣ኢትዮጵያ

4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በጨረታው መከፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 3 በተገለፀው አድራሻ የካቲት 06 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) በባንክ የተመሠከረለት የከፍያ ማዘዣ (CPO) ከቴክኒክ መጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለዘጠና (90) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።

7. የጨረታው ጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለስልሳ (60) ቀናት ይሆናል።

8. ግሩፑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *