የእብናት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለእብናት ከተማ አስ/መ/ል/ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የዉሃ እቃዎች፣ የማሽን ኪራይ ማለትም ዶዘር፣ ግሪደር፣ ሎደር እና ገልባጭ መኪና ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማስቀረብ ይፈልጋል


Be’kur(Feb 02, 2026)

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የእብናት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለእብናት ከተማ አስ/መ/ል/ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የዉሃ እቃዎች ሎት 2 የማሽን ኪራይ ማለትም ዶዘር ፣ግሪደር ፣ሎደር እና ገልባጭ መኪና ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማስቀረብ ይፈልጋል።

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ።

  1. የ2018 የበጀት አመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
  4. ለማሽን ተወዳዳሪዎች በስማቸዉ የባለቤትነት ሊብሬ ያላቸዉ መሆን አለበት፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ድምር አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) በእብናት ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በማሰራት በጥሬ ገንዘብ እብናት ከተማ ገ/ጽ/ቤት ዋና ገ/ያዥ ገቢ በማድረግ ገቢ የሆነበትን የገቢ ደረሰኝ ከኦርጅናል የጨረታ ሰነዱ ጋር ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን ዋና በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ውስጥ አድርጎ እብናት ከተማ ገ/ጽ/ቤት/ግዥና ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 02 ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 03 መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታው ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ቢገኙም ባይገኙም በግዥና ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 02 ጨረታው በወጣ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 እስከ 4፡00 ታሽጎ 4፡10 ላይ ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜ፣ እሁድ እና በዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች በሰነዱ የተዘረዘሩት እቃዎችን በሙሉ የመሙላት ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡ የአንድንም የእቃ ዋጋ ዝርዝር አለሞሙላት ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፡፡
  9. አሸናፊው የሚለየው በጥቅል ድምር ይሆናል፡፡
  10. የሚገዙ እቃዎችና አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን ) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ (ሰነዱ ላይ የተጠቀሰ እቃ መሰረዝ መደለዝ ከጨረታ ውጭ ያስደርጋል፡፡
  11.  ተጫራቾች የአሸነፏቸውን እቃዎችና ማሽኖች መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  12. አቅርቦቶች ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 03 መግዛት ይችላሉ፡፡
  13. አሸናፊው በተጠየቀው ስፔስፊኬሽን መሰረት ጥራቱ ተጠብቆ ካላቀረበ በመመሪያ መሰረት መ/ቤቱ እርምጃ ለመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. አሸናፊው አሸናፊነቱን እንደተገለፀለት በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እብናት ከተማ ገ/ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መውሰድ አለበት፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኙ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
  16. መ/ቤቱ በዝርዝሩ የተጠቀሱትን እቃዎች ብዛት 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
  17. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመምጣት መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የእብናት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት