Your cart is currently empty!
የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የመድሀኒት አይነቶችን፣ የተለያዩ የህትመት አይነቶችን፣ እስቴሽነሪ (አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎችን) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Be’kur(Feb 02, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት
- ሎት1. የተለያዩ የመድሀኒት አይነቶችን ከEPSS እና ከሚዴክስ የመድሀኒት አቅራቢ ድርጅቶች ሊገኙ በማይችሉበት ጊዜ ሲጠየቁ ከ5-10 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ድረስ ሊያቀርቡ የሚችሉ ተጫራቾችን ለ6ወር ብቻ፣
- ሎት2. የተለያዩ የህትመት አይነቶችን ፣
- ሎት3. እስቴሽነሪ (አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፍኬት እና ከመንግስት የሚጠበቅባቸዉን የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸዉ ማስረጃ የግብር ክሊራንስ እና በመድሀኒት ግዥ ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች ሜዲካል ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የግዥዉ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ) እና በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ስለጨረታው አጠቃላይ ዝርዝር መግለጫ (እስፔስፊኬሽን) እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ከግ/ፋ/ን/ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 3 መዉሰድ የሚቻል ሲሆን ጨረታዉ በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛዉ ቀን ድረስ እስከ 11፡30 ብቻ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ በፊት ልዩ ልዩ ምክንያት በሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ያልታገዱ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸዉን በአማርኛ ቋንቋ ማንኛውንም የመንግስት ግብር ያካተተ ሆኖ የጨረታ ሰነዱ በፖስታ ታሽጎ የድርጅቱ ክብ ማህተም ፤ፊርማ እና አድራሻ ማስቀመጥ አለባቸዉ፡፡ በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ማድረግ የለባቸዉም፡፡ የጨረታ ሰነዱን ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ ) ለህትመት ግዥ እና ለእስቴሽነሪ (አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ) የሞሉትን ጠቅላላ ድምር አንድ በመቶ እና ለመድሀኒት ግዥ 30,000 (ሰላሳ ሽህ ብር) በማስያዝ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ / ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሆስፒታሉ የጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ገቢ በማድረግ ከፖስታው ውስጥ አብሮ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸዉ ከታወቀ ለህትመት ግዥ እና ለእስቴሽነሪ (አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ የሞሉትን ጠቅላላ ድምር 10በመቶ እና ለመድሀኒት ግዥ 100,000 (አንድ መቶ ሽህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሆስፒታሉ የጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ታትሞ ይቆይና በ16ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም ፕሮግራሙ የማይስተጓጎል ይሆናል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የመንግስት የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ዉድድሩ የሚለየዉ የመድሀኒት አይነቶችን በተናጠል ሲሆን ህትመትና እስቴሽነሪ በሎት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የተጠየቁ እቃዎችን ሆስፒታሉ በሚሰጠው እስፔስፊኬሽን እና ሳምፕል መሰረት በጥራት በማቅረብ በራሳቸው ትራንስፖርት እስከ ሆስፒታሉ ድረስ በማምጣት የሚያስረክቡ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱየተጠበቀ ነው፡፡ለበለጠ መረጃ 058 827 04 27 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል