Your cart is currently empty!
የደብቡ ጐንደር አስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚዉሉ የችሎት ካባ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰፋት ይፈልጋል
Be’kur(Feb 02, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደብቡ ጐንደር አስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚዉሉ የችሎት ካባ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰፋት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉና በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በዘመኑ ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በሎት ከጠቅላላ ዋጋ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከጠቅላላ ዋጋው ላይ አንድ በመቶ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ
አለባቸው፡፡ - ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ደ/ጐን/ዞን/ከፍ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 35 በመቅረብ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሠነዱ ጋር በፖስታ ውስጥ አሽጐ ማቅረብ ከጨረታ ውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡ ገንዘቡም ቢጠፋ መ/ቤቱ ሊጠየቅ አይችልም፡፡
- መ/ቤቱ ለመግዛት የሚፈልገውን እቃዎች አይነት ዝርዝር የያዘ ሠነድ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 35 በመምጣት እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ አድርገው ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ቢሮ ቁጥር 35 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑም በ15ኛዉ ቀን 11፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ተወካዩች ቢገኙም ባይገኙም የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛዉ ቀን 2፡30 ቢሮ ቁጥር 35 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት የሚመረጠዉ ወይም የሚለዩት በጥቅል ዋጋ ነዉ፡፡
- አሽናፊ ድርጅት የአሸናፈዉን እቃ ደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች ሰነድ በሚገዙበት ጊዜ ኦሪጅናል እና ኮፒ ፈቃድ በመያዝ ሰነዱን በአካል ወይም በህጋዊ ወኪላችዉ አማካኝነት ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ ለመረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 03 86 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደቡብ ጐንደር አስተዳደር ዞን ከፍ/ፍ/ቤት