የጭልጋ ወረዳ ገ/ኢ/ኮ/ል/ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Be’kur(Feb 02, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጭልጋ ወረዳ ገ/ኢ/ኮ/ል/ጽ/ቤት ለጭ/ወ/ሀ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በመደበኛ እና በcmp project ድጋፍ ለእጅ ዉሃ ጉድጓድ አገልግሎት የሚውሉ

  • ሎት 1 የዉሃ እቃ መሳሪያዎች፣
  • ሎት 2 ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ኤሌክትሮኒክስ እንዲሁም
  • ሎት 3 ለግንባታ አገልግሎት የህንጻ መሳሪያዎችና አገሮሰቶን ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

 ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1.  በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸዉ የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3.  የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የግዥዉ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. የሚገዙ የዕቃዎች ዓይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሸን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6.  በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚፈለግባቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒዉን በጀርባዉ ላይ ከዋናዉ ጋር ተገናዝቧል ብሎ በመፃፍ ማህተም፣ ስም፣ ፊርማና ቀን በማስቀመጥ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ ቢሮ ቁጥር 7 ከረዳት ገ/ያዥ ድረስ በመምጣት መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ አንድ በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ በመክፈል ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም በሲፒኦ ከሆነ በባንክ የተረጋገጠ ሲሆን ሲፒኦዉ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  9. ማንኛዉም ተጫራች የሚጫረቱበት ዋጋ በተዘጋጀዉ ሰነድ ላይ በመሙላት አንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ፖስታዎች ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ላይ ስማቸዉንና አድራሻቸዉን በመፃፍ በጭልጋ ወረዳ ዉስጥ ከግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ዉስጥ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ፖስታዉን እስከተገለፀዉ ቀን ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በ16ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡ ጨረታዉ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ግ/ፋ/ንብ/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ዉስጥ ጨረታዉ ይከፈታል፡፡
  10. ጨረታው 16ኛዉ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል፡፡
  11.  ለሁሉም ምድቦች አሸናፊዎች አሸናፊነታቸዉ እንደተገለፀላቸዉ ቅሬታ ከማቅረቢያ ጊዜ በተጨማሪ ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ዉል በመዉሰድ ጭ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ድረስ ዕቃዎቹን በጥራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ተጫራቾች በሌላ ዋጋ ላይ ተተርሰዉ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
  13. አሸናፊዎች የዉል ማስከበሪያ 10 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  14. ጨረታዉ ከመከፈቱ በፊት መቅረብ ያለበት ማስተካከያ ካለ ከ10 ቀናት በፊት ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  15. አሸናፊዎች የሁሉም ምድብ ዕቃዎች የሚያቀርቡት ጭ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ድረስ በራሳቸዉ ወጭ ይሆናል፡፡
  16. ተጫራቾች ለዉድድር ከቀረቡ በኃላ ሀሳባቸዉን መለወጥ /ማሻሻል/ ራሳቸዉን ማግለል አይችሉም፡፡
  17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  18. ጨረታዉ ሲሞላ ሥረዝ ድልዝ ካለዉ ጨረታዉ ሙሉ በሙሉ ዉድቅ ይሆናል፡፡
  19. የጨረታ አሸናፊዉን የምንለየዉ በጥቅል ድምር ይሆናል፡፡
  20. ለበለጠ መረጃ ከግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 333 11 57 ወይም 09 12 08 05 89 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፦ የጨረታ ሰነዱ ሲሞላ ሁሉንም አይተሞች መሞላት አለባቸዉ ክፍት መሆን የለበትም እንዲሁም በየገፁ የድርጅትዎ ማህተምና ፊርማ ይደረግበት፡፡

የጭልጋ ወረዳ ገ/ኢ/ኮ/ል/ጽ/ቤት