Your cart is currently empty!
ፀደይ ባንክ አ.ማ. የድርጅት ቤት ለመሸጥ ይፈልጋል
Be’kur(Feb 02, 2026)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ፀደይ ባንክ አ.ማ ለአቶ የኔጌጥ ምናየሁ ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዘውን በአማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር አዘና ከተማ በካርታ ቁጥር 615/11 በአዋሳኝ በምሥራቅ የማ/ቦታ፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን አምሳሉ አበራ እንዲሁም በደቡብ ብርሃኑ ሁነኛው የሚያዋስኑት የተበዳሪው ንብረት የሆነ የድርጅት ቤት በአዋጅ ቁጥር 97/90 በአዋጅ ቁጥር 216/92 እንደተሻሻለ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በጨረታ መነሻ ብር 3,035,344.79( ሶስት ሚሊዮን ሰላሳ አምስት ሺህ ሶስት መቶ አርባአራት ብር ከሰባዘጠኝ ብር) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ደንቦችና ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ እንጋብዛለን፡፡
- ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ ኛውን በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ በፀደይ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ መስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው የሚሳተፈው በሕግ ሰውነት ያገኘ ሰው ከሆነ የድርጅቱን መመስረቻ ጽሑፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ ሕጋዊ ሰውነት ያገኘበትን የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ሕጋዊ ውክልና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ፀድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈልና በጨረታ
ያሸነፈውን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ አሸናፊው በ15 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ - በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ይመለስላቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ ቫትን ጨምሮ ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማንኛውንም ወጭዎች ይሸፍናል፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሆኖ ለቀረው የሊዝ ክፍያ ገዥ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል፡፡
- ጨረታው የካቲት 26/2018 ዓ.ም በፀደይ ባንክ አማ እንጅባራ ዲስትሪክት ከጠዋቱ 3፡00-6፡00 ይደረጋል፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ቤቱን ለመጎብኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 18 58 93 29 በመደወልና ቀጠሮ በማስያዝ በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ፡፡
ፀደይ ባንክ አ.ማ