Your cart is currently empty!
200 ካ.ሜ ቦታ ላይ ያረፈ መኖሪያ ቤት የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
Be’kur(Feb 02, 2026)
የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ/ከሳሽ አቶ ክንዴ ይግዛው እና በአፈ/ተከሳሽ እነ ፋሲል ምትኩ መካከል ስላለው የገንዘብ ክርክር ጉዳይ፤ በተከሳሽ ፋሲል ምትኩ ባለቤት ወይም ሚስት በሆነችው በወ/ሮ ሳራ ካሳሁን ዘላለም ስም ተመዝግቦ የሚገኝ፤ በባሕር ዳር ከተማ በአጼ ቴዎድሮስ ክ/ከተማ በማራኪ ቀበሌ 200 ካ.ሜ ቦታ ላይ ያረፈ መኖሪያ ቤት ከጥር 25/2018 ዓ.ም ጀምሮ በጋዜጣ ታትሞ ቆይቶ፤ የካቲት 26/2018 ዓ.ም በግልጽ ጨረታ ስለሚሸጥ፤ መጫረት የምትፈልጉ በእለቱ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 መጫረት የምትችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የባሕር ዳር ከተማ ወ/ፍ/ቤት