Your cart is currently empty!
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ አላቂ የፅህፈት ዕቃዎች እና የስልጠና መርጃ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የስራ ቱታ እና የሽልማት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 05, 2026)
የደቡብ ዕዝ የጨረታ ማስታወቂያ
የማስታወቂያ ቁጥር ደቡብ ዕዝ ግዥ A-2/2018
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- አላቂ የፅህፈት ዕቃዎች እና የስልጠና መርጃ ዕቃዎች
- የፅዳት ዕቃዎች
- የስራ ቱታ
- የሸልማት ዕቃዎች
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች በጨረታው ሊወዳደር ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው የጨረታ ዓይነቶች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ / ከፋይነት / ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ::
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ለእያንዳንዱ ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መመሪያ መሠረት በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚመረቱበትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ የዕቃውን ዓይነት ኢንቨሎፑ ላይ በግልፅ መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከተጫራቾች ዝርዝር መምሪያ ጋር የማይመለስ ብር 400.00 በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታውጆ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት ቀናት ውስጥ ቶጋ መከላከያ ሠራዊት ካምፕ በሚገኘው የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ግዥ ቢሮ መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቶጋ መከላከያ ሠራዊት ካምፕ በሚገኘው ደ/ዕዝ ጠ/መምሪያ ግዥ ቢሮ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ደ/ዕዝ መምሪያ ግዥ ቢሮ ጎን በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈፅሙ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: ያሸነፉበትን ዕቃ በራሳቸው ትራንስፖርት ወጭ በማጓጓዝ እና በማራገፍ ቶጋ መከላከያ ሠራዊት ካምፕ በሚገኘው የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ግምጃ ቤት ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ እንዲሁም 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046-328-0020 ይደውሉ
የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
ቶጋ