በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት ሊያስገነባው ለፈለገው የግንባታ ሥራ አማካሪ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 06, 2026)

የምክር አገልግሎት የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አ.ማ 004/2018 ዓ.ም

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት ሊያስገነባው ለፈለገው የግንባታ ሥራ አማካሪ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል። በመሆኑም ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን፣ የሰው ኃይል በማቅረብ የሚሠሩ ደረጃቸው ከዚህ በታች በተጠቀሰው መስፈርት በማሟላት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

ሎት

የሥራው አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና

ደረጃ

 

የጨረታ ሰነድ መሸጥ የሚጀመርበት ቀን

የጨረታ ማስገቢያ ቀን

የጨረታ መክፈቻ ቀን

ሎት 1

ወረዳ 07 አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ጥገና ሥራ

 

ከተደራጁበት ወረዳ ዋስትና ደብዳቤ

 

ጥቃቅን አነስተኛ ዘርፍ ልዩ ደረጃ 1 አማካሪ ማኅበራት

በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት 2:30-10:00 ሰዓት

 

በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ድረስ

በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከ4፡15 ሰዓት ጀምሮ

ሎት 2

ወረዳ 01 የልብስ መቀየሪያ ጂ+0 ግንባታ ሥራ ወረዳ 06 የልብስ መቀየሪያ እና አዳራሽ ስራ

ከተደራጁበት ወረዳ ዋስትና ደብዳቤ

 

ጥቃቅን አነስተኛ ዘርፍ ልዩ ደረጃ 1 አማካሪ ማኅበራት

በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት 2:30-10:00 ሰዓት

በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ድረስ ብቻ

በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከ4፡15 ሰዓት ጀምሮ

አማካሪዎች ድርጅቶች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሕጋዊ ዶክሜንታችሁን ዋናውንና አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።

2. በዘርፉ የ2018 ዓ.ም የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3. ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ ምስከር ወረቀት ያላቸው፤

4. ማንኛውም ስራ ተቋራጭ ከፌደራል ከተማ ልማት እና ኮንሰትራክሽን ሚኒስቴር የምስክር ወረቀት ያላቸው እና ከአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ እና ፍቃድ ቁጥጥር ባለሥልጣን ተመዝግቦ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ሳይዝ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።

5.ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናዉን (original) እና የማይመለስ ቅጂ (copy) ይዞ በመቅረብ በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳዳር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የምህንድስና ግዥ ቡድን 5ኛ ፎቅ ቀርበው ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ። ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው የሥራ ቀን በእለቱ ባለቤቱና ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በጽ/ቤቱ ከሰዓት 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡15 የሚከፈት ይሆናል።

6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ከተደራጁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ግዴታ አለበት። የቀረበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ያለበት በቴክኒካል ኦርጂናል ሰነድ ውስጥ ወይም ከፖስታው ውጪ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ፤ፋይናንሽያል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም የታሸገውን 6 ፖስታ በአንድ እናት ፖስታ የድርጅቱን ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የስራ አይነት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። የጨረታው ፋይናንሻል ሰነድ ላይ ያልተፈረመ ሆኖ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የተስተካከለ ዋጋ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ ከጨረታው ያሰርዛል።

8. ተጫራቾች የሥራዎችን የዋጋ ዝርዝር እና የጨረታ መወዳደሪያ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና አድራሻቸውን በማስፈር ማህተም አድርጎ ኢንቨሎፑን በማሸግ ማስታወቂያው በወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳዳር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የምህንድስና ግዥ ቡድን 5ኛ ፎቅ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እሰከ 4፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በአራዳ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት ምንም አይነት ውል ያላቋረጡ መሆንይጠበቅባቸዋል።

10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድን ከማስገባታቸው በፊት የተጫራቾችን መመሪያ (Instruction to Bidder (ITB) and Scope of Consultancy service) እንዲያነቡ ይመከራል።

11. አማካሪው ድርጅት የዲዛይን ማሻሻያ፣ የግንባታ ክትትል እና የውል ማስተዳደር ስራ ይሰራል።

12. አማካሪ ድርጅቱ ስራውን በጥራት ለማከናወን የሚከተላቸውን መሠረታዊ ስራቴጂዎች የሚያቀርብ፤ እነዚህም ባለመፈጸማቸው ተጠያቂ እንደሚያደርገው ማረጋገጫ የጻፈና በስራ አስኪያጅ ወይም በኃላፊው የተፈረመ ሆኖ ማህተም ያለው ሰነድ የሚያቀረብ መሆን አለበት።

13. አሰሪው መ/ቤት አሸናፊው ካሸነፈበት አጠቃላይ የስራ መጠን 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይቻላል።

14. አሸናፊ ተጫራች በስራ ዝርዝር ላይ ከገበያ ዋጋ በጣም ከፍ ያለ እና ዝቅ ያለ ዋጋ ከሞላ (Cost Break Down) ያቀርባል።

15. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የድርጅቱ የስራ ልምድና ማንኛውም በቴከኒካል የተጠየቁት ዶክመንቶችን አሰሪ መ/ቤት ኦርጂናል ዶክመንት ከሰጠው አካል የማጣራት መብት የተጠበቀ ነው።

16. ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ጀምሮ በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት የምሕንድስና ግዥ ቡድን 5ኛ ፎቅ ይከፈታል። የጨረታው መከፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።

17. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ አራት ኪሎ በሚገኘው በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳዳር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት የምሕንድስና ግዥ ቡድን 5ኛ ፎቅ በግንባር በመቅረብ መረዳት ይችላሉ።

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት የመንግሥት ግዢ አስተዳደር ቡድን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *