በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግዥታ ስራዎች ጽ/ቤት ሊያሰራው ለፈለገው ስራ በግንባታ ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 06, 2026)

የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ተቋ 003/2018 ዓ.ም

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግዥታ ስራዎች ጽ/ቤት ሊያሰራው ለፈለገው ስራ በግንባታ ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም ለግንባታ አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን የሰው ሃይል በማቅረብ የሚሰሩ በጥቃቅን አነስተኛ ዘርፍ ተመራቂ ማህበራትንና በጥቃቅን አነስተኛ ተመራቂ ማህበራትን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ለማሠራት ይፈልጋል።

ተቋራጮች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

ሎት

የስራዉ አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና

ደረጃ

የጨረታ ሰነድ መሸጥ የሚጀመርበት ቀን

የጨረታ ማስገቢያ ቀን

የጨረታ መክፈቻ ቀን

ሎት 1

ወረዳ 07 አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ጥገና ስራ

100,000 ሺህ ብር

ጥቃቅንና አነስትኛ ዘርፍ ተመራቂ ማህበራት

በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት  2:30-10:00 ሰዓት

በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ድረስ ብቻ

በጋዜጣው ከወጣበት በ16ኛው 4፡15 ጀምሮ

ሎት 2

የወረዳ 01 የልብስ መቀየሪይ ጂ+0 ግንባታ ስራ

ከተደራጁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤ

በጥቃቅንና አነስትኛ መብቃት

በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት  2:30-10:00 ሰዓት

በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ድረስ ብቻ

በጋዜጣው ከወጣበት በ16ኛው 4፡15 ጀምሮ

ሎት 3

የወረዳ 06 የልብስ መቀየሪያ ጂ+1 ግንባታ ስራ እና አዳራሽ ግንባታ ስራ

50,000 ሃምሳ ሺህ ብር

ጥቃቅንና አነስትኛ ዘርፍ ተመራቂ ማህበራት

በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት  2:30-10:00 ሰዓት

በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ድረስ ብቻ

በጋዜጣው ከወጣበት በ16ኛው 4፡15 ጀምሮ

1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ህጋዊ ዶኩሜንታችሁን ዋናውንና አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።

2. በዘርፉ የ2018 ዓም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚቐሎና፣ ከስራ ከሎት ቢሮ የታደሰ የዕድገት ደረጃ የምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚይስችል ቃስ ከሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3. ከመንግስት ግዢና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤

4. ማንኛውም ስራ ተቋራጭ ከፌዴራል ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የምስክር ወረቀት ያላቸው እና ከአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ እና ፍቃድ ቁጥር ባለስልጣን ተዘግቦ የታደለ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ሳይዙ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።

5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዚ በአየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት 2:30 እስከ 10፡00 ድረስ ከተራ ቁ.14 ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናዉን (original) እና የማይመለስ ቅጂ (copy) ይዞ በመቅረብ በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳዳር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የምህንድስና ግዢ ቡድን 5ኛ ፎቅ ቀርበው ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ።

6. ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው የሥራ ቀን በእለቱ ባለቤቱና ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በጽ/ቤቱ ጠዋት 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 4፡15 የሚከፈት ይሆናል።

7. ማንኛውም ተጫራች ለ60 ቀናት የሚያገለግል የጨርቅ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ በባንክ የክፍያ ተዕዛዝ (CPO) Unconditional bank Guarantee ወይም የባንክ ከላይ በተጠቀሰው የብር መጠን ማቅረብ ግዴታ አለበት። የቀረበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ያለበት በቴክኒካል ኦርጂናል ሰነድ ውስጥ ወይም ከፖስታው ውጪ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

8. አሰሪው መ/ቤት አሸናፊው ካሸነፈበት አጠቃላይ የስራ መጠን 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይቻላል።

9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድን ከማስገባታቸው በፊት የተጫራቾችን መመሪያ (Instruction to Bidder (ITB) እንዲያነቡና የግንባታ ሳይቱን እንዲመለከቱ ይገደዳሉ።

10. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ፤ ፋይናንሽያል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም የታሸገውን ፖስታ በአንድ እናት ፖስታ የድርጅቱን ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የስራ ፕሮጀክት አይነት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። እንዲሁም የጨረታው ፋይናንሻል ሰነድ ላይ ያልተፈረመ ሆኖ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የተስተካከለ ዋጋ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ ከጨረታው ያሰርዛል። በተጨማሪም በስራ ዝርዝር በሙሉም ሆነ በአንድ የስራ አይተም ላይ ዋጋ አለመሙላት ከተገኘ ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል።

11. ተጫራቾች የሥራዎቹን የዋጋ ዝርዝር እና የጨረታ መወዳደሪያ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን እና አድራሻቸውን አስፍሮ ማህተም በማድረግ ኢንቨሎፑን በማሸግ ማስታወቂያው በወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳዳር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የምህንድስና ግዥ ቡድን 5ኛ ፎቅ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እሰከ 4፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል።

12. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በአራዳ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት ምንም አይነት ውል ያላቋረጡ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

13. አሸናፊ ተጫራች በስራ ዝርዝር ላይ ከገበያ ዋጋ በጣም ከፍ ያለ እና ዝቅ ያለ ዋጋ ከሞላ (Cost Break Down) ያቀርባል።

14. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የድርጅቱ የስራ ልምድና ማንኛውም በቴክኒካል የተጠየቁት ዶክመንቶችን አሰሪ መ/ቤት ኦርጂናል ዶክመንት ከሰጠው አካል የማጣራት መብት የተጠበቀ ነው።

15. ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣበት በ16ኛው ተከታታይ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ጀምሮ በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳዳር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የምህንድስና ግዥ ቡድን 5ኛ ፎቅ ይከፈታል። የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።

6. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ አራት ኪሎ በሚገኘው በአራዳ ክፍስ ከተማ አስተዳዳር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የምህንድስና ግዥ ቡድን 5ኛ ፎቅ በግንባር በመቅረብ መረዳት ይችላሉ።

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *