Your cart is currently empty!
በአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የልደታ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት የፅዳት ዕቃ እና የፅሕፈት መሣሪያ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 06, 2026)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የልደታ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት የፅዳት ዕቃ፣ የፅሕፈት መሣሪያ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ በመስኩ ለተሰማራችሁ ግለሰቦች (ድርጅቶች) የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡
በዚሁ መሠረት፦
1. የፅዳት ዕቃ፣ የፅሕፈት መሣሪያ ግዥ ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማራችሁ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ እና በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ክሊራንስ እና የE.G.P (Electronics Government Procurement) ተመዝጋቢ መሆኑን
2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የፅዳት ዕቃ ብር 3,000.00፤ የፅሕፈት መሣሪያ ብር 5,000.00 በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ብቻ በአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የልደታ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅ/ፅ/ቤት ስም በማሠራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
3. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መመሪያ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ተከታታይ የሥራ ቀናት ጠዋት 2፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ‘ጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል በጽ/ቤታችን የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ማግኘት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸው በመግለጽ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ተከታታይ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ግዥ ቡድን ቢሮ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
5. ጨረታው በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጐ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
6. ቅ/ጽ/ቤቱ ቅዳሜ እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ የሚሠራ ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበትን ቀን በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ማግኘት የሚቻል ሆኖ ቅዳሜ እንደ ሙሉ ቀን ይቆጠራል፡፡
7. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል (የመወዳደሪያ ዋጋ የተሞላበት ሰነድ) ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንቶችን (የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ኦርጅናልና እና የተጠየቁ አስፈላጊ የንግድ ፍቃዶችና መረጃዎች ኮፒ) ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ውስጥ በማድረግ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው፡፡
9. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የተሰጠውን ዋጋ ለማሻሻል፣ ለመለወጥ ወይም ትቼዋለሁ ማለት አይችልም፡፡
10. ማንኛውም ተጫራች ማጭበርበር ወይንም ሙስናን በተመለከተ በኢትዮጵያ ሕጎች የተደነገገውን የሚያከብር መሆን ይገባዋል፡፡
11. ጨረታውን ለማዛባት ሙከራ የሚያደርግ ተጫራች ከጨረታው እንደሚሰረዝ እና ወደፊትም እንዳይሳተፍ እንደሚታገድ እንዲሁም ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንደሚወረስበት ማወቅ ይኖርበታል፡፡
አድራሻ፡– ልደታ ክ/ከተማ ልደታ ፍርድ ቤት ተስፋ ኮከብ አጠገብ አስተዳደርና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 604
ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ. 0118 494 257 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ
በአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የልደታ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት