የአንድነት ፓርክ የመኪና መቆሚያ ህንጻ (ፓላስፓርኪንግ) ለቢሮ አገልግሎት ወይም ለሱቅ መሸጫ የሚሆን ክፍሎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 06, 2026)

ለቢሮ ወይም ስሱቅ አገልግሎት የሚውል
የኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 3/2018

የአንድነት ፓርክ የመኪና መቆሚያ ህንጻ (ፓላስፓርኪንግ) ለቢሮ አገልግሎት ወይም ለሱቅ መሸጫ የሚሆን ክፍሎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፦

1. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. ተጫራቾች ዋጋ ሞልተው የሚያቀርቡበት ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዞ በቀረበው ሰነድ ቅደም ተከተል መሰረት ቫትን ጨምሮ ነው፣

3. ተጫራቾች የቦታውን ግምት በካሬ በተቀመጠው የመነሻ ዋጋን ተንተርሶ የሚቀርብ ይሆናል፣

4. ተጫራቾች የሚያሸንፉበትን ቦታ ላይ ለሽያጭ የሚቀርቡበትን ዕቃና አገልግሎት ዋጋ እንዲሁም የድርጅታቸውን ሙሉ ፕሮፋይል ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

5. እያንዳንዱ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ በጽ/ቤቱ ስም ማስያዝ ይኖርበታል፣

6. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በጽ/ቤቱ እንግዳ መቀበያ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፣

7. እያንዳንዱ ተጫራች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፣

8. እያንዳንዱ ተጫራች ከተሰማሩበት ንግድ ሥራ ዘርፍ ውጪ በሆነ ንግድ ፍቃድ መወዳደር አይችሉም ፣

9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 ሰአት ተዘግቶ በዕለቱ ከሰዓት 8:15 ሰዓት ይከፈታል፣

10. ፓርኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።

ለተጨማሪማብራሪያ ስልክ ቁጥር +25111-1-54-31-03 /+251118578718/ +25111653007 ፋክስ ቁጥር 226292
በጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *