Your cart is currently empty!
የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ቋሚና አላቂ ዕቃዎች እና የአገልግሎት ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 06, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር አ/አ/ከ/ፍ/ቤት/02/2018
የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቋሚና አላቂ ዕቃዎች እና የአገልግሎት ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች
- ሎት.2. አላቂ የጽዳት እቃዎች
- ሎት.3. የደንብ ልብስ
- ሎት.4. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ሎት 5. የተለያዩ የህትመት ስራዎች
- ሎት.6. የኤልክትሮኒክስ እና ማሽነሪ ጥገና ስራዎች
- ሎት.7. የተለያዩ የቧንቧ ስራዎች ዝርጋታ እና የጥገና ስራዎች
- ሎት.8. የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ እና ጥገና ስራዎች
1- የግዥ መለያ ቁጥር አ/አ/ከ/ፍርድ ቤቶች 02/2018
2. ግዥው ግልጽ ጨረታ ነው
3. ጨረታ ሰነድ የወጣበት ጥር ወር 2018 ዓ/ም
ተጫራቾች ህጋዊ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆኑ፤ የተጨማሪ እሴት የታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት እና የጨረታ መሳተፊያ ደብዳቤ የሚያቀርቡ ላሸነፉበት እቃ የውል ማሰከበሪያ ማሲያዝ የሚችሉ እንዲሁም ቋሚ የስራቦታ ወይንም ድርጅት ያላቸው ሆነው በቅድመ ምልከታ ወቅት ድርጅታቸውን ወይንም የሥራ ቦታቸውን ለማሳየት ፍቃደኛ የሆኑ ከዚህ በፊት በፍርድ ቤቱ ጨረታ አሸንፈው በገቡት ውል መሰረት ግዴታቸውን የተወጡ ድርጅቶች ብቻ።
1. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ከግዥ ፈጻሚ የአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ቢሮ 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ ለተገለፁት ዕቃዎች ለተወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ (C.P.O) ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት ከጠቅላላ ዋጋ 2% ፐርሰንት ወይም ተጫራቾች በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ ያደራጃቸው መስሪያ ቤት ለዋስትናው በፍርድ ቤቱ አድራሻ የተጻፈ ደብዳቤ የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ ያደራጃቸው መስሪያ ቤት ለዋስትናው በፍርድ ቤቱ አድራሻ የተጻፈ ደብዳቤ ለጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው የሚወዳደሩበትን በየሎቱ ለየብቻ በማድረግ በግልጽ ኢንቨሎኘ ላይ ሎቱን በመፃፍ እና የድርጅቱ ማኅተም እና ፊርማ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰአት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚያው እለት 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መከፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
4. ተጫራቾች ናሙናቸውን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት እስከ 4 ሰዓት ድረስ ለሚጫረቱበት በሰነዱ ላይ ናሙና እንዲቀርብ ለተጠየቀባቸው እቃዎች በጨረታው ለመወዳደር ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩት ዕቃዎች የእያንዳንዱን ነጣላ ዋጋ እና ዋጋ እና ድምር ዋጋ VAT ጨምሮ ማካተት ይኖርባቸዋል። ፍርድ ቤቱ ጨረታውን ለመገምገም የሚጠቀምባቸው መስፈርቶች ዕቃዎቹ ፍርድ ቤቱ ባስቀመጠው ስፔስፊኬሽን መሰረት ወይም በሚቀርበው ናሙና ጥራት፤ ዋስትና ፤ አነስተኛ ዋጋ እና አጠቃሎ የማቅረብ ጊዜ ግምት ውስጥ ይገባል።
5. ፍርድ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
6. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
7. በየሎቱ የሚሳተፉ ተወዳዳሪ ድርጅቶች በዘርፉ የሚሰሩ ድርጅቶች ብቻ መሆን አለባቸው።
8. ኮፒ እና ኦሪጅናል ኢንቨሎፕ በተናጠል (ለየብቻ) በፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መስፋርት የማያሟሉ አቅራቢዎች ከጨረታው ውጪ የሚደረጉ ይሆናል።
አድራሻ
ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሜክሲኮ ፍሊፕስ ህንጻ አጠገብ የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ላይ አዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 102 ሲሆን ስልክ ቁጥር 011-515-7040
የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች