Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የንግድ ቤት(ሱቅ) ኪራይ ለማከራየት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 06, 2026)
የንግድ ቤት(ሱቅ) ኪራይ በድጋሚ የወጣ
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ብግጨ /ኢኢኮ/R3-01/2018
የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አዲስ አበባ ስታዲዬም አከባቢ ከግዮን ሆቴል ጎን ካለው የሜድሮክ ናኒ ህንጻ አጠገብ የሚገኘውን ህንጻ ለቢሮ አገልግሎት ለመጠቀም የህንጻ እድሳት አድርጎ የጨረሰ ሲሆን በህንጻው ስር የሚገኘውን አንድ ክፍል ለንግድ ሥራ ወይም ለቢሮ አገልግሎት ለማከራየት ይፈልጋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከታች በተገለፀው አድራሻ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 19 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 4፡00 ሰአት ድረስ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ። ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም። በጨረታው ላይ ለመገኘት በፈለጉ ተጫራቾች ወይም የተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው የካቲት 19 ቀን 2018 ዓ.ም በ4:30 ሰአት ይከፈታል።
- ከጨረታ ሰነድ ጋር የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና ቲን ሰርተፍኬት መያያዝ አለበት።
- በጨረታው አሸናፊ ድርጅት ቅድሚያ ክፍያ ለስድስት (6) ወር የሚከፍል ይሆናል።
- የጨረታ አሸናፊዎች የኪራይ ውል መዋዋል የሚችሉት ለጨረታ ባስገቡት የንግድ ፈቃድ ስም ብቻ ነው።
- በጨረታ ያሸነፉበትን ክፍል በምንም ዓይነት ለሌላ ወገን ስም ማዞርም ሆነ ተከራይቶ ማከራየት የማይቻል ሲሆን፤ ይህንን ለማድረግ የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጪ እንደሚሆኑ እና የኪራይ ውሉ እንደሚሰረዝ ለማሳሰብ እንወዳለን።
- ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000237347262 ገቢ በማድረግ የባንከ ደረሰኝ ይዘው በመምጣት ወይም በአካል ቀርበው በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ይህ የጨረታ መጋበዣ ሰነድ የሚያካትተው የሚከራየው ቦታ ዝርዝር እና ቦታውን በካሬ የሚያሳይ ዲዛይን ይሆናል።
- ይህ የኪራይ አገልግሎት ጨረታ ታሳቢ የሚያደርገው በሀገር ውስጥ ለሚፈፀም የአገልግሎት ሽያጭ (የምክር አገልግሎትን አይጨምርም) የሚውል መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይሆናል።
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-
የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን(ኢኢ.ኮ.) ሕንጻ 1 አራተኛ ፎቅ በኮርፖሬት አገልግሎቶች የግዥ ቡድን ቢሮ፣ ከመገናኛ አደባባይ ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ በሚወስደው ዋና ቀለበት መንገድ ወደ አደይ አበባ ስታዲዬም
(የኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት ማእከል) የሚያስገባው መገንጠያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የሚሰጥበት ህንጻ
ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ስልክ ቁጥር +251 11 618 7446
አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን