Your cart is currently empty!
በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ሪጅን ለጂንካ ቅ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 07, 2026)
የቤት ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 09/2018
በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ሪጅን ለጂንካ ቅ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
1. የሚከራየው ቤት ሙሉ ግቢ ሆኖ ለመዝገብ ቤት የሚሆን አንድ ሰፋ ያለ ክፍል (ስፋቱ ቢያንስ ከ6×4 ሜትር) ያላነሰና ሌሎች ተጨማሪ 10 ያህል ለቢሮ አመቺ የሆኑ ስፋታቸው ቢያንስ ከ3×4 ያላነሱ ከፍሎች ያሉት መሆን ይኖርበታል፤
2. የኪራዩ ጊዜ ከሚያዝያ 01 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ ለሶስት አመት የሚቆይ ይሆናል።
3. የክፍያው ሁኔታ በስምምነት በየ 6 ወሩ ወይም በአመት አንድ ጊዜ በቅድሚያ ክፍያ የሚፈጸም ይሆናል፤
4. ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢዎች ከሆኑ የማስረጃው ኮፒ አብሮ መቅረብ አለበት፤
5. ቤቱ ህጋዊና የመንግስት ግብር እየተከፈለበት ያለ ስለመሆኑ ማስረጃ ያለውና የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫው ኮፒ ሆኖ አብሮ መቅረብ ይኖርበታል፤
6. ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ገዝተው የሚያከራዩበትን የአንድ ወር ዋጋ በመሙላትና በታሸገ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 – 11፡00 ሰዓት ድረስ በጂንካ ቅ/ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
7. ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው እለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሳጥኑ ይከፈታል፣
8. የጨረታው ውጤት በሪጅን ጽ/ቤት(ሀዋሳ) በኩል ተከፍቶና ተወስኖ የሚገለጽ ይሆናል።
9. ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡– ሪጅን ጽ/ቤት(ሀዋሳ) ስልክ ቁጥር 046 221 4317 ወይም 046 221 4140 ጂንካ ቅ/ጽ/ቤት ጂንካ ሆስፒታል ፊትለፊት፣ ማዘርላንድ ክሊኒክ አጠገብ
ስልክ ቁጥር 09 04 84 09 90 / 09 17 74 84 80
በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ሪጅን ጂንካ ቅ/ጽ/ቤት