በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውሃ፤ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ የኔትወርክ መሠረተ ልማት ዕቃ አቅርቦት እና ዝርጋታ ለአውቶሜሽን ሥራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 07, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውሃ፤ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለመንግስት ስራ አገልግሎት የሚውል ፡ የኔትወርክ መሠረተ ልማት ዕቃ አቅርቦት እና ዝርጋታ ለአውቶሜሽን ሥራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ተጫራቾች በንግድ ሥራ ዘርፍ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ያላቸውን ማስረጃዎቻቸውን በግልፅ ሊነበብ በሚችል አደራጅተው ማቅረብ አለባቸው።

  • ተጫራቾች በአቅራቢነት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ 15 ተከታታይ በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ20ኛው ቀን እስከ ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የሚገባ ሲሆን ከቀኑ 8፡30 ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
  •  ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመከፈል ከቢሮው ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 203 ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር ብቻ በባንክ በተመሰከረለት / CPO/ የባንክ ጋራንት ማስያዝ ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋ /ፕሮፎርማ/ ኦርጅናል ቴክኒካል ዶክመንት እና ኦርጅናል ፋይናንሻል ዶክመንት ለየብቻው በማሸግ ቴክኒካል ኮፒ እና ፋይናንሻል ኮፒ በማድረግ እንዲያቀርቡ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ድረስ በታሸገ ፖስታ በቢሮ ግዥ ፋንብ አሰ ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 201 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይችላሉ። CPO ከቴክኒከ ዶክመንት ጋር አንድ ላይ መሆን አለበት።
  • ለሁሉም ዕቃ የማቅረቢያ ጊዜ አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀ በኋላ በ20 ቀን የሚያቀርቡ ይሆናል።
  • ተጫራቾች የሰጡትን ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ጊዜ ጀምሮ ለ45 ቀን መሆን አለበት።
  •  / ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር፡-046 212 8953

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የውሃ፣

ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *