Your cart is currently empty!
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ የእንሰሳት መድሀኒት እና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 07, 2026)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 09/2018
ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው እንሰሳት ሃብት ልማት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የእንሰሳት መድሀኒት እና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መካፈል የምትፈልጉ፡-
- ተጫራቾች በዘርፋ የተሰማሩበትን ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር / TIN No/ ያላቸውና ከብር 200000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ዋጋ ባላቸው ግዥዎች የሚሳተፋ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገበ እና ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ።
- መድሃኒቶቹን በአንድ ጊዜ በአይነት፤ በመጠን በጥራት ሳያጓድል ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ስማቸውን አድራሻቸውን በመጻፍ እና በመፈረም የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋና እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 40,000 በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ክሬዲት ወይም ገንዘብ ጽ/ቤት በመሂı ያስያዙበትን ደረሰኝ ከኦርጅናል ዋጋ ማቅረቢያ ውስጥ መያያዝ አለበት። የእቃ ግዥ መ/ቤቱን፣ የተጫራቾችን ስምና አድራሻ፣ እንዲሁም የግዥውን የእቃ አይነት በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛ ቀን ከሰአት 8፡00 ሰዓት ድረስ በጽ/ቤቱ በተዘጋጀው ሳጥን ውሰጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በዚሁ እለት በ16ኛው ቀን ከሰአት 8:00 ሰዓት ይታሸግና በእለቱ 8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም።
- 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልዋለ ጨረታው በሚቀጥለው በመንግስት የሥራ ቀን ይከፈታል።
- መ/ቤቱ ጨረታውን የሚያወዳድረው በነጠላ ዋጋ ነው።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት።
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን መድሃኒት እና እቃ በራሱ ትራንስፖርት አን/ጠ/ወ/ ንብረት ክፍል ድረስ በመውሰድ ማስረከብ ይጠበቅበታል።
- የጨረታ ሰነዱን በአን/ጠ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚታሸግበት ቀን ድረስ በመንግስት የስራ ሰአት ለእያንዳነዱ ሰነድ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ/ ብር መግዛት ይችላሉ።
- በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለፀ በተጫራቾች መመሪያ እና በኦርጅናል ሰነዱ ላይ በዝርዝር ስለሚገለጽ ዝርዝራቸውን በትኩረት ማየት ይጠበቅባቸዋል።
- ማንኛውም የመድሃኒት አይነት የአገልግሎት ጊዜው 2 አመት እና ከዚያ በላይ መሆን አለበት።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጽ/ቤቱ የሚገኘው ከአ/አበባ በስተሰሜን 110 ኪ/ሜ ርቀት በደ/ብረሃን መስመር ላይ ነው።
- ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 011-632-0147 ወይም 011-632-0745 ደውለው ይጠይቁ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት