Your cart is currently empty!
በዘመን ኮንስትራክሸን ኮርፖሬሽን ምስራቅ አማራ ማስ/ጽ/ቤት ስር ለሚገኘው ለእሚኮ ቢሮ ግንባታ ፕ/ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የሳንተሪ እቃዎች አቅርቦት እንዲሁም የገጠማ ስራዎችን ህጋዊና ብቃት ካላቸው አቅራቢዎች በነጠላ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 07, 2026)
በድጋሜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በዘመን ኮንስትራክሸን ኮርፖሬሽን ምስራቅ አማራ ማስ/ጽ/ቤት ስር ለሚገኘው ለእሚኮ ቢሮ ግንባታ ፕ/ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የሳንተሪ እቃዎች አቅርቦት እንዲሁም የገጠማ ስራዎችን ህጋዊና ብቃት ካላቸው አቅራቢዎች በነጠላ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ፡–
1. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት እቃ ዘርፍ ላይ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የማንኛውም የግዥ መጠን ከብር 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤ ከብር 20 ሺህ በላይ ለሆነ ግዥ የቫት 15% ግማሹን /50%/ እና ከተከፋይ ሂሳብ ላይ 3% ዊዘ ሆልዲንግ ታከስ ይቆረጣል፡፡
2. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የአገልግሎት ዓይነት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በዘን የምስራቅ አማራ ማስ/ጽ/ቤት በደሴ ከተማ በአስተዳደርና ፋይናንስ ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 16 እና ዘመን አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ ለአንድ የጨረታ ሰነድ በብር 300.00 መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት አልቆ በ16ኛው ቀን በዘመን ምስራቅ አማራ ማስ/ጽ/ቤት/ደሴ ከተማ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ይከፈታል፤ ተጫራቾች በእለቱ ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡ ያልተገኘ ተጫራችም በጨረታ ሂደቱ ተገዥ ይሆናል፡፡
4. ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደሩበትን የእቃ ዓይነት ስፔስፊኬሽን አይቶ በትክክል ዋጋ በመሙላት የሚጫረቱበትን ዋጋ በአንድ ወይም ወጥ በሆነ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማዘጋጀት በጥንቃቄ በታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖስታ/ ደሴ ከተማ በሚገኘው በዘመን ምስራቅ አማራ ማስ/ጽ/ቤት ግዥ ኦፊሰር ቢሮ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ከማሸጊያው ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. ማንኛውም ተጫራቾች ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2%/ሁለት ፐርሰንት/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /cpo/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
7. አሸናፊው ሲታወቅ ላሸነፈው እቃ የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /በcpo/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማስያዝ ያሸነፈውን እቃ በራሱ ትራንስፖርት መጫኛና ማውረጃ እና የቴስት ማሰሪያ ወጭን ጨምሮ ተጫራቹ ችሎ የእቃውን ጥራት በአማካሪ በማረጋገጥ እና ቴስት ለሚያስፈልጋቸው ግብአቶች ቴስት በማሰራት ማለፉ በአማካሪ በማረጋገጥ ያሸነፈውን እቃ ፕሮጀክቱ በሚገኙበት መጋዘን ድረስ ገቢ ማድረግ ግዴታ ነው።
8. ማንኛውም ተጫራች ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ማቅረብ እንዳለበት ተገንዝቦ ዋጋ መሙላትና መወዳደር ያለበት ሆኖ የሚሞላው የ1 ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በሚሸጠው ጨረታ ሰነድ ዋጋ መሙያ ፎርም መሰረት ቫትን ያካተተ መሆን ሲገባው በእስክርቢቶ ቫት ይጨመርበት ተብሎ ከተጻፈ ተጫራቹ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
9. በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ እንዳይኖር በጥንቃቄ ይሞላ፡፡ በአጋጣሚ ስርዝ ድልዝ ከተፈጠረም ፓራፍ ይደረግ። ተጫራቾች እኩል ዋጋ በሚያቀርቡበት ጊዜ 1ኛ ብዛት ላሸነፈው ቅድሚያ ይሰጣል እንደዛም ሆኖ እኩል ከሆኑ በእለቱ በተገኙት ተጫራቾች ፊት በእጣ ይለያል፡፡ ተጫራቾ ካልተገኘም እጣው በኮሚቴው ይጣላል፡፡
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ሆኖ ተጫራቹ በዚህ ምክንያት ለሚያወጣው ወጪ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስ.ቁ 033 112 4973 / 033 311 1009 ወይም 0111 265 652 አ/አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ይጠይቁ።
አድራሻ፡– ደሴ ካራ ጉቱ ግብርና ፊትለፊት ከሚገኘው ምስ/አማ/ማስ/ጽ/ቤት፣ አ.አ ለገሀር አመልድ ህንጻ 7ኛ ፎቅ ዘመን አ.አ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት
በዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የምስራቅ አማራ ማስ/ጽ/ቤት