Your cart is currently empty!
አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ የንግድ ቤት ኪራይ ለማከራየት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 07, 2026)
በድጋሜ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር የንግድ ቤት ኪራይ 06/2018
አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 103/1990 እና በማሻሻያ አዋጅ 807/2005 መሰረት የካፒታል እቃ ፋይናንስ ስርዓት ለማቅረብ የተቋቋመ እና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የስራ ፈቃድ የተሰጠው የፋይናንስ ተቋም ሲሆን በአራዳ ክ/ከተማ ከጊወርጊስ ቤተክርስቲያንወደ 6 ኪሎ በሚወስደው መንገድ ድንበሬ መታሰቢያ ህንጻ ጎን የሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት ህንጻ ውስጥ 1ኛ እና 2ኛ ፎቅ ያሉትን ቦታዎችን፣ ለሚኩራ ክ/ከተማ ሰሚት ሳይት የሚገኝ 40/60የንግድ ቤት፣ ቦሌ ክ/ከተማ ቱሪስት እና ቦሌ ቡልቡላ ሳይት የሚገኙ 40/60 የንግድ ቤቶችን ለካፌ እና ሪስቶራንት እንዲሁም ለተለያዩ አገልግሎቶች ለማከራየት ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ጋብዘናል።
- ተጫራቾች ተወዳድረው ባሸነፉበት ቤት ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ለማውጣት፣ ቤቱን ተከትሎ የተጠቀሙበትን የውሀ እና የመብራት ፍጆታ ለመከፈል እና የአካባቢውን ሰላም የሚያደፈርስ ስራ ለመስራት ፍቃደኛ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በዋናው መ/ቤት ህንጻ ለ1ኛና 2ኛ ፎቅ ቤቶች ለእያንዳንዱ ቤት የጨረታ ማስከበሪያ 30,000 (ሰላሳ ሺ ብር) እንዲሁም ለ40/60 የንግድ ቤቶች ለእያንዳንዱ ቤት 6000 (ስልሳ ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 24/2018 ዓ.ም የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ወደ 6 ኪሎ መሄጃ ድንበሬ መታሰቢያ ህንጻ ጎን በሚገኘው አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 5ኛ ፎቅ፣ ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ፋይናሽያል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ እስከ የካቲት 24/2018 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በቀን 24/6/2018 ዓ.ም በ4፡00 ተዘግቶ በእለቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ ኢማ 4ኛ ፎቅ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል።
- ኩባንያው ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተከርስቲያን ወደ 6 ኪሎ መሄጃ ድንበሬ መታሰቢያ ህንፃ ጎን
አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ