የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ለመብራት ዝርጋታ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 07, 2026)

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ለመብራት ዝርጋታ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ተጫራቾች

1. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል ክሊራንስ፣ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ ለሚያቀርቡት ዕቃ ከኢትዮጵያ የተስማሚነትና ምዘና ድርጅት ብሄራዊ የደራጃዎች ምልከት የመጠቀም የታደሰ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል እና በጨረታ ለመሳተፍ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው::

2, የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ሥራ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ወይም ሂሳብ ክፍል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ቅዳሜና እሁድ የመስሪያ ቤቱ የስራ ቀናት አይደሉም።

3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 የሥራ ቀናት ውስጥ በጨረታ ሰነዱ ላይ ለተጠቀሱት ዕቃዎች ዋጋ ዝርዝር በመሙላት በአገልገሎቱ ዋና /ቤት የግዥ ቡድን ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ እስከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የተጫራቾች ዋጋ በግልጽ የሚነበብና ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን ይኖርበታል፡፡ ስርዝ ድልዝ ያለበት የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 7ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 430 ይከፈታል፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት /Refugees & Returnees Service/ በሚል የተዘጋጀ የባንክ ማዘዣ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች ሁለት ሰነዶች ማለትም ቴክኒካል ፕሮፖዛል እና ፋይናንሽያል ዝርዝር የያዘ ሰነድ ለየብቻ በማሸግ አገልግሎት መስሪያ ቤቱ በሚያዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

7. የጨረታው አሸናፊ ጥሪ በደረሰው 05 /አምስት/ ቀናት ውስጥ በአገልግሎቱ ዋና /ቤት ቀርቦ የሥራ ውል መፈረም አለበት፡፡

8. አሸናፊው ጥሪ በደረሰው በአምስት ቀናት ውስጥ በአገልግሎቱ ዋና /ቤት ቀርቦ ውል ካልፈረመ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመ/ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡

9. የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ፡የእንቁላል ፋብሪካ አደባባይን ሳይሻገሩ ከፌዴራል ፖሊስ ክበብ ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር 09-97-23-66-31

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *