ደቡብ ወሎ ዞን ውሃና ኢነርጂ መምሪያ የኤሌክትሮ መካኒካል ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 07, 2026)

ሀገር አቀፍ የግልጽ ረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ወሎ ዞን ውሃና ኢነርጂ መምሪያ ሎት 1 የኤሌክትሮ መካኒካል ዕቃዎች  ግዥ ለወረኢሉ ወረዳ ሰኞ ገበያ፣ለደላንታ ወረዳ ወገልጤና እና ለከላላ ወረዳ ቲርቲራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት መወዳደር ይችላሉ።

  1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው
  3. የተሰጠውን ፈቃድ ለሌላ ሰው ወይም ድርጅት አሳልፈው ያልሰጡ፣
  4. ኤሌክትሮን መካኒካል እቃዎች ግዥ በተመለከተ በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው፣
  5. የገዥ መጠኑ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  6. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እና 2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
  7. ተጫራቾች ኦርጅናል ዕቃ መሙላት እና ያሸነፉባቸውን ዕቃ በባለሙያ ማስፈተሽ አለባቸው።
  8. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይቻላል።
  9. ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ሲሞሉ ከእያንዳንዱ የዕቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ መሙላት አለባቸው።
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁፕር 601 ማግኘት ይቻላል።
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1.5% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
  12. ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ ሊያሲዙ በመምሪያው የገቢ ደረሰኝ ቆርጦ ኮፒውን ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር መታሸግ አለበት።
  13. አሸናፊው አካል የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የሚያስዝ ይሆናል።
  14. ውድድሩ የሚካሄደው በጠቅላላ ድምር በሎት ነው።
  15. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ በግዥ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 610 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን መግዛትና በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  16. ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብ/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 610 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ይታሸጋል። በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4:30 ይከፈታል። የመክፈቻው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ከጠዋቱ 400 ሰዓት ታሽጎ 430 ይከፈታል።
  17. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 610 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 033 111 6134  በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 033 111 8118/19 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
  18. በመ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ  የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የደቡብ ወሎ ዞን ውሃና ኢነርጂ መምሪያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *