Your cart is currently empty!
ሕብረት ባንክ አ.ማ. መኖሪያ ቤት በግልፅ ሐራጅ(ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል
Reporter(Feb 08, 2026)
የሐራጅ ማስታወቂያ፤
ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፉ በኩል ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዘውንና ከዚህ በታች የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ(ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል::
|
የተበዳሪ ስም
|
የአስያዥ ስም
|
አበዳሪው ቅርንጫፍ
|
ቤቱ የሚገኝበት አድራሻና የቦታ ስፋት |
የንብረቱ የይዞታ ማረጋገጫ ቁጥር
|
የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር
|
ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
|
አቶ ብርሃኑ ጫላ ጨንዶ
|
አቶ ብርሃኑ ጫላ ጨንዶ |
አምቦ
|
ኦሮሚያ ክልል፣ አምቦ ከተማ፣ ያኢ ገዳ ቀበሌ፣ የቦታ ስፋት 200 ካ.ሜ፣ አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤት |
WBILBMA/3061/015
|
1,701,289.00 |
መጋቢት 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ስዓት
|
የሐራጅ ደንቦች፡-
1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ.(Hibret Bank SC) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ::ከባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም::
2. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከቅርንጫፉ ወይም ከሕግ አገልግሎት መምሪያ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት በፊት መጎብኘት ይችላል::
3. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ተበዳሪ እና አስያዥ ብቻ ናቸው::
4. ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል::ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት::
5. ሐራጁ የሚካሄደው ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ላይ ነው::
6. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል::
7. ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል::ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች ደግሞ ያቀረበውን ዋጋ ባንኩ ሲቀበለው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል የሚገልፅ ደብዳቤ የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል::በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል::
8.ከፍ ሲል የተጠቀሰውን ንብረት ለሚገዛና የባንኩን የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መመዘኛዎች ለሚያሟላ ተጫራች በሚሰጠው ከፍተኛ ዋጋ ላይ ባንኩ 50%(ሃምሳ በመቶ) ብድር ያመቻቻል::
9. የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች የጨረታ አሸናፊ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ይከፍላል::
10. ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
11. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር- አምቦ ቅርንጫፍ፡ 0112 60 99 84/14 ወይም የሕግ አገልግሎት መምሪያ፡ 0114 70 03 15/47/4103 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል::