ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እና ርችት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 08, 2026)

በድጋሚ የወጣ ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2018

ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ

  • ሎት አንድ ኤሌክትሮኒክስ እና
  • ሎት ሁለት፡ ርችት አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ሥለሆነም

.

የዕቃው ዓይነት

መለኪያው

ምርመራ

1

ሎት አንድ ኤሌክትሮኒክስ

በቁጥር

የሎት 1 የሎት 2 ዕቃዎች ብዛት እና ዓይነት ዝርዝር መረጃ በተመለከተ በጨረታ ሰነዱ ላይ ያገኙታል

2

ሎት ሁለት፡ርችት

በቁጥር

ተጫራቾች የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበት አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የአቅራቢዎች የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣እና ሌሎች ያሏቸውን ማስረጃዎቻቸውን በግልፅ ሊነበብ በሚችል መልኩ አደራጅተው ማቅረብ አለባቸው።

  • ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ በሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል ከግዥ/ፋንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ሎግታ አጠገብ ሲዳማ ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ፣ ቢሮ ቁጥር 18 ሀዋሳ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ 20,000.00 ሃያ ሺህ ብር በባንክ የተመሰከረለት CPO ብቻ ለእያንዳንዳቸው ሎት ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋ /ፕሮፎርማ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ዶክመንት ኮፒና ኦርጅናል በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የሥራ ቀናት ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ጨረታው ከታወጀበት እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  • ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10ኛው ቀን ከቀኑ 800 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 830 ሰዓት ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ//ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 18 ሲዳማ ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ሎግታ አጠገብ ሀዋሳ ይከፈታል
  • /ቤቱ ከጠቅላላው የግዥ መጠን (ብዛት) ላይ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
  • /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ነገር ግን የጨረታው ሳጥን የሚታሸግበት እና የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ባይሆን የጨረታዉ ሳጥን የማሸጉም ሆነ የመከፈት ሥነሥርአት የሚከናወነው በቀጣይ የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት እና ቦታ ይሆናል

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0916025922 ወይም 0912462506 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *