Your cart is currently empty!
በማ/ኢ/ክ መንግሥት ሀዲያ ዞን ሌሞ ፋ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ሪቮለረቭግ ፈንድ ለእንስሳት ህክምና አገልግሎት የሚውል መድሃኒት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 08, 2026)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በማ/ኢ/ክ መንግሥት ሀዲያ ዞን ሌሞ ፋ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ሪቮለረቭግ ፈንድ ለእንስሳት ህክምና አገልግሎት የሚውል መድሃኒት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለምፈልግ፡–
1. በመስኩ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው
2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ ያላቸው
3. የቫት ተመዝጋቢነት ሠርትፍኬት ያላቸው
4. የአቅራቢነት ፈቃድ ያላቸው ተወዳዳሪዎች ሀሳባቸውን በፖስታ በማሸግ ሀድያ ዞን ሌሞ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 14 በአካል በማቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ በመክፋል መግዛት ይችለሉ።
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናውን 10000 /አሥር ሺህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ይሆናል። የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ በአሃዝና በፊደል ይጻፋል። ዋጋው ቫትን ያካተተ መሆን አለበት። በአሃዝ የተጻፈው ግልጽ ካልሆነ በፉደል የተጻፈው ተቀባይነት ይኖረዋል።
ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ የመወዳደሪያ ሰነድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ጋር ከላይ የተገለጸውን ማስረጃዎች ጭምር በፖስታ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 14 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል። ጨረታውም 10ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ስዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በዕለቱ አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጎጉለውም።
ማሳሰቢያ፡–
መ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
በማ/ኢ/ክ መንግሥት ሀዲያ ዞን ሌሞ ፋ/ጽ/ቤት