Your cart is currently empty!
ተስፋ ድርጅት የተለያዩ ማቴሪያሎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Reporter(Feb 08, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ተስፋ ድርጅት በሲቭል ማህበራት ኤጄንሲ የተመዘገበ ህጋዊ ድርጅት ሲሆን በአገራችን በተለያዩ ክልሎች ማለትም በጋምቤላ፣ ቤንሻንጉል፣ በኦሮሚያ፣ በአማራና ሲዳማ ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ ባሉት ቅርንጫፎች በትምህርት፣ በሙያ ሥልጠና እና በተለያዩ የልማት ሥራዎች የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ወገኖች አገልግሎት ይሰጣል።
ድርጅቱ ለሚያከናዉናቸዉ ተግባራት ግብዓት የሚሆኑ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማቴሪያሎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
No |
Item |
Qty. |
|
1 |
Desk top computer |
32 |
|
2 |
Laptop Computer |
8 |
|
3 |
Printer (all in 1Colour Pinter) |
3 |
|
4 |
Photocopy Machine |
2 |
|
5 |
LCD Projector |
3 |
|
6 |
Digital Industrial sublimation printer process |
1 |
|
7 |
Inkjet printer (Garment) |
1 |
|
8 |
Video Camera (5D Mark IV) with Tripod |
1 |
|
9 |
Sound recorder |
1 |
|
10 |
External Hard disk |
4 |
|
11 |
Network toolkit |
1 |
|
12 |
4×8 Flatbed laser CNC-engraving cutting machine |
1 |
|
13 |
4in 1 light duty combination machine (Wood Work) |
1 |
|
14 |
Dust blower |
1 |
|
15 |
Computer maintenance tool |
1 |
ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እንዲሁም ተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርቲፊኬት ያለው።
2. የግብር መለያ ቁጥር (in No.) ሰርቲፊኬት
3. ተጫራቾች የሚያስገቧቸውን የዋጋ ሰነዶች የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶኩመንት ለየብቻ በማሸግ ወይም ለየብቻ ያሸጉትን በአንድ ፖስታ በማሸግ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 የስራ ቀናት እስከ የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 6፡00 ድረስ አየር ጤና ተስፋ ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 (አምሣ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ በድርጅቱ ስም አሰርቶ ከቴክኒካል ዶኩመንቱ ውስጥ በማስገባት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8:00 ሰዓት ይከፈታል።
6. ተጫራቶች የተዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ አየር ጤና ከሚገኘው ዋናው ቢሮ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመግዛት መውሰድ ይችላሉ። ዋጋ ማቅረብ የሚቻለው በተዘጋጀው ፎርም ብቻ ነው። ማንኛዉም ስርዝ ድልዝ ተቀባይነት የለዉም።
7. ተጫራጮች የሚያቀርቡት ዋጋ እስከ ማስረኪቢያ ቦታ (ተስፋ ድ ር ጅ ት አየር ጤና ዋና መስሪያ ቤት ድረስ) ያለውን የትራንስፓርት ዋጋ ጭምር የያዘ መሆን አለበት።
8. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ተስፋ ድርጅት ዋናው መ/ቤት
አየር ጤና ሳሚ ካፌ ፊት ለፊት
ስልከ ቁጥር – 011 369 4480 / 011 693 691
አዲስ አበባ