Your cart is currently empty!
አዲስ ዓለምአቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል አ.ማ የማስታወቂያ ስራ አገልግሎት ግዢ እና የህግ ማማከር አገልግሎት ግዢ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Reporter(Feb 08, 2026)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር አዓኮማ አ.ማ 07-08/2018
አዲስ ዓለምአቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል አ.ማ ደረጀውን የጠበቀ የማስታወቂያ ስራ አገልግሎት ግዢ እና የህግ ማማከር አገልግሎት ግዢ ለመፈፀም በመስኩ ሰፊ ልምድ፣ ብቃት እና ችሎታ ያላቸውን ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል::
|
ሎት ቁጥር |
የሚገዛው እቃ/አገልግሎት |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን |
|
ሎት 1 |
የማስታወቂያ ስራ አገልግሎት ግዢ |
50,000 |
|
ሎት 2 |
የህግ ማማከር አገልግሎት ግዢ |
30,000 |
- ተጫራቾች ለስራው ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ከገቢዎች ሚኒስቴር ጨረታ ለመሳተፍ የተሰጠ ክሊራንስ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት ማስረጃ፣ ከሚመለከተው ባለስልጣን መ/ቤት የተሰጠ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣ በኋላ ከየካቲት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት (ምድብ) ብር 300 (ሶስት መቶ) በአካውንት ቁጥር 1000616070839 በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል አ.ማ ጽ/ቤት ገቢ በማድረግ ያስገቡበትን ደረሰኝ በመያዝ ከቢሮ ቁጥር 313 ተገኝተው መውሰድ ይችላሉ::
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት የመወዳደሪያ ዝርዝር ፍላጎት መግለጫ እና ዋጋ ሞልተው ዋናውንና ኮፒውን በሁለት ፖስታ ( ቴክኒካል እና ፋይናሻል) በታሸገ ኢንቨሎፕ ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ በማድረግ፣ የሚጫረቱበትን ሎት በፖስታው ላይ በመጻፍ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው:: ጨረታው የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት አገልግሎት ዓይነት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የባንክ ክፍያ ማዘዣ (C.P.O) ለአዲስ ዓለምአቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል አማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ኩባንያው ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
እዲስ–ዓለም እቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል አ.ማ
አድራሻ፡– ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ሲ ኤም ሲ አደባባይ ፀሀይ ሪል እስቴት ፌት ለፌት
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0116 670082
cttx Advertising and Promotion cttx, cttx Art cttx, cttx Audio Visual, cttx Billboards and Digital Advertising cttx, cttx Consultancy cttx, cttx Event Organizing and Planning cttx, cttx Legal cttx, cttx Other cttx, cttx Public Address Systems cttx, cttx Public Relations cttx, Photography and Filming Service and Equipment cttx