Your cart is currently empty!
ዘብሩክ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ የተለያዩ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 08, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር B–ETH 01/26
ዘብሩክ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በቁጥር፡0883 የተመዘገበ መንግስታዊ ያልሆነ ግበረሰናይ ድርጅት ሲሆን ከተመዘገበበት ጊዜ ጀምሮ ዋና ቢሮውን አዲስ አበባ በማድረግ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ የድርጅቱ አላማ የጋማ እንስሳትን ደህንነትና ጤንነት ማሻሻል እና በእነዚህ የጋማ እንስሳት ጉልበት ኑሯቸውን የመሰረቱ የማህበረሰብ ክፍሎችን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ሲሆን ይህንንም ለመተግበር ከመንግሰት እንስሳት እና የግብርና ተቋማት ጋር በትብብር ይሠራል።
ድርጅታችን ዘብሩክ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዘርፉ የተሰማሩ፣ ብቁ እና መስፈርቾችን የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ ይሆናል።
|
S/N |
Item Description |
Unit |
Qty |
Remark |
|
1 |
Jackets for Men with Brooke Logo |
Pcs |
253 |
Local |
|
2 |
Umbrellas (TOP)for women with Brooke Logo |
Pcs |
90 |
|
|
3 |
Umbrellas (TOP) for men with Logo |
Pcs |
160 |
|
|
4 |
Short leather boots for men (6 holes) |
pair |
253 |
Local |
|
5 |
Scarf for women |
pcs |
98 |
|
- ተጫራቾች ህጋዊና የዘመኑ የታደሰ ፈቃድ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የተሟላ የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የቤት ቁጥር 797 ከሚገኘው የድርጅታችን ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው የጨረታ ዋጋቸው 2% ቦንድ በሲፒኦ መልክ ብቻ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሲፒኦው የጨረታ ኤንቨሎፕ ውስጥ ለብቻው ታሸጎ መቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች በሰም የታሸገውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 7 ቀናት ውስጥ ከላይ በተ.ቁ 2 በተጠቀሰው አድራሻ በሚገኘው የብሩክ ፅ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰአት በ7 ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ነው፡፡ የጨረታ ማቅረቢያው 7ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀናት ከዋለ የጨረታ መዝጊያው ቀን በሚቀጥለው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ይሆናል፡፡
- ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ውጭ የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- የጨረታው ተጫራቾቸ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋበት ቀን (በተ.ቁ.4 የተመለከተው) ከቀኑ በ8 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የጨረታ መክፈቻውን ቀን የማራዘም ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-661-0069/011 662-1885 በመደወል ወይም
በኢሜይል info@thebrookeethiopia.org አድራሻችንን መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻችን 22 በአውራሪስ ከቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል በጀርባ ባስው የኢትዮጵያ
ንግድ ባንክ በኩል ወደ 24 በሚወስደው መንገድ ሳደ በንጋት ህንፃ እና በአዳነ ገብሩ ህንፃ በኩል ወደ ውስጥ ገባ ብሎ::
ዘብሩክ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ