Your cart is currently empty!
ዝግባ የህጻናትና አረጋውያን መርጃ የበጎ አድራጎት ድርጅት የ2017/2018 (እ.ኤ.አ የ2025) በጀት ዓመት የነበረውን የሂሳብ እንቅስቃሴ በጨረታ አወዳድሮ ለማስመርመር ይፈልጋል
Reporter(Feb 08, 2026)
የሂሳብ ምርመራ /ኦዲት ስራ/ ጨረታ ማስታወቂያ
ዝግባ የህጻናትና አረጋውያን መርጃ የበጎ አድራጎት ድርጅት ከ3,254 በላይ ለከፋ ችግር የተጋለጡ ሕፃናት፣ ጧሪ ያጡ አረጋዊያንና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ችግረኛ ሴቶች በአዲስ አበባ፣ በባህርዳር እና እንጅባራ ከተማ የድጋፍና እንክብካቤ አገልግሎት እየሰጠ ያለ ማኅበረሰብ አቀፍ አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው።
በመሆኑም ድርጅቱ የ2017/2018 (እ.ኤ.አ የ2025) በጀት ዓመት የነበረውን የሂሳብ እንቅስቃሴ በጨረታ አወዳድሮ ለማስመርመር ይፈልጋል።
በመሆኑም፡–
1. በሂሳብ ምርመራ ስራ ተሰማርተው የሚሰሩ፣
2. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ናምበር/ እና ሌሎች አስፈላጊና ህጋዊ መረጃዎች ያሏቸው።
3. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ዋጋ በፖስታ በማሸግ ቀበሌ 02 ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 500.00 /አምስት መቶ/ በባንክ በተራጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
5. ከአሁን በፊት ምርመራ ካደረጉባቸው መ/ቤቶች የተሰጠ ማስረጃ መቅረብ የሚችሉ።
6. ጨረታው ከፍት ሆኖ የሚቆየው ከጥር 26/2018 ዓ.ም እስከ የካቲት 11/2018 ዓ.ም ከቀኑ በ10፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል::
7. ጨረታው የሚከፈተው በእለቱ የካቲት 11/2018 ዓ.ም በ10:30 ይሆናል።
8. በተጨማም አስፈላጊ መረጃዎችን ከጨረታ ማስገቢያ ቀን በፊት ቢሮ ድረስ በመቅረብ መመልከት ይቻላል።
ለበለጠ መረጃ፦ በ0912056999/0984292929 ይደውሉ።