Your cart is currently empty!
የደራርቱ ቱሉ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 08, 2026)
ለሁለተኛ ጊዜ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ 002/2018
የደራርቱ ቱሉ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች
ማለትም፦
- የደንብ ልብሶች
- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- አላቂ የትምህርት ዕቃዎች
- አላቂ የፅዳት ዕቃዎች
- ልዩ ልዩ መሣርያዎች
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል በዚህ መሰረት ተጫራቾች፡–
1. በመንግስት ዕቃ አቅራቢነት : ተመዝግበው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች በዘርፉ ወይም በመስኩ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው።
3. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቅያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በትምህርት ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር10 ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረብያ ቦታ በግልጽ በመሙላት በመጨረሻ ቦታ ላይ ስም ፤ ፊርማና ህጋዊ ማህተም በማኖር በታሸገ ኢንቨሎፕ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በማሸግ ይህ ማስታወቅያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ 2፡30-11፡00 ዋጋቸውን በመሙላት በተጠቀሰው የስራ ሰዓት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
7. ለጨረታ ማስከበርያ ሎት 1) 5884.76 ሎት 2) 22167.98 ሎት 3) 19559.56 ሎት 4) 21058.04 ሎት 5) 217850.17 ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
8. ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው ሊዘጋ አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
9. ጨረታውን አሸናፊ ሆነው ከተገኙ በኋላ 10% ባሸነፉበት ዕቃ መጠን መሰረት የውል ማስከበርያ ማስያዝ ይኖርቦታል።
10. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክር ከጨረታው ውጪ እንደሚሆንና የጨረታውን ማስከበርያ CPO እንደሚወረስባቸው ማወቅ አለባቸው።
11. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ ቀን ከቀኑ በ5፡00 ሰዓት በትምህርት ቤቱ የግ/ፋይ/ንብ/አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል።
12. መስርያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 011 434 3278/ 011 471 5349
14. ጥቃቅንና አነስተኛ በሃገር ውስጥ ምርት ላይ የተሳተፉ ስለመሆኑ በቂ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ካልሆነ ግን እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ገዝተው እና CPO አስይዘው መወዳደር ይኖርባቸዋል።
አድራሻ፡– በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት ከቃሊቲ ቶታል ዝቅ ብሎ ከአሮጌው አስፓልት 200 ሜትር ገባ ብሎ
የደራርቱ ቱሉ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት