የጥበብ እድገት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት የ2018 ዓ/ም የትምህርት እቃዎች፤ የደንብ ልብስ እና ሌሎች አላቂ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች በ3ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 08, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጥበብ እድገት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት የ2018 ዓ/ም የትምህርት እቃዎች፤ የደንብ ልብስ እና ሌሎች አላቂ እቃዎች የፅዳት እቃዎች በ3ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች ጨረታውን መወዳደር ትችላላችሁ::

1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ. እንዲሁም በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ  መሆን አለባቸው፡፡

2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በት/ቤቱ ግ/ፋ/ን/አስ በመገኘት የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነድ በት/ቤቱ ግቢ ቢሮ ቁጥር G+1/005 በመምጣት መግዛት ትችላላችሁ:: ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት ግልፅ በሆነ መንገድ ቫትን አካቶ በመሙላት ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ቢሮ ቁጥር G+1/005 ኦርጅናል እና ኮፒውን ማስገባት አለባችሁ ::

3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን ቢሮ ቁጥር G+1/005 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡ 30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

5. ት/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባችሁ ::

7. ተጫራቾች ዋጋ መሙላት ያለባቸው ት/ቤቱ ባዘጋጀው ሰነድ ብቻ ነው :: አድራሻ፡- በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ ዐ4 ከወ/ሮ ቀለም ወርቅ መሰናዶ ት/ቤት ከፍ ብሎ ያዳም ዘውድ ሆቴል አጠገብ 100 ሜትር ገባ ብሎ

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-0111119306/0913436612
የጥበብ እድገት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *