Your cart is currently empty!
Justice for All – Prison Fellowship Ethiopia (JFA-PFE) የፈሳሽ ሳሙና ማቀላቀያ ማሽኖች (Mixing Machine) ለመግዛት ለህጋዊ እና ተወዳዳሪ አቅራቢዎች የግልፅ ጨረታ ያቀርባል
Reporter(Feb 08, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
Justice for All – Prison Fellowship Ethiopia (JFA-PFE) ለትርፍ ያልተቋቋመ እና በኢትዮጵያ ውስጥ በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት በቀን 30/01/2012 በመዝገብ ቁጥር 1327 በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ዳግም ተመዝግቦ ሕጋዊ ሰውነት ተሰጥቶት የሚሰራ አገር በቀል ድርጅት ነው። በጀርመን BMZ በሚደገፍ ፕሮጀክት፣ እና በኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች ኮምሽን ትብብር የሚፈፀም የገቢ ማስገኛ (IGA) ፕሮጀክት በማከናወን ላይ ይገኛል።በመሆኑም፤ በሶስት ማረሚያ ቤቶች በሕግ-ጥላ ስር ለሚገኙ ሴት ታራሚዎች የሙያ ስልጠና እና ገቢ ማስገኛ የሶስት ዓመት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያነት እንዲረዳ የፈሳሽ ሳሙና ማቀላቀያ ማሽኖች (Mixing Machine) ለመግዛት ለህጋዊ እና ተወዳዳሪ አቅራቢዎች የግልፅ ጨረታ ያቀርባል።
1. የጨረታው ዓይነት
- 500 ሊትር የፈሳሽ ሳሙና ማቀላቀያ ማሽን
- ብዛት: 3 (ሶስት)
ማሽኖቹ የሚተከሉባቸው ቦታዎች:
- ገለምሶ ማረሚያ ቤት
- ጭሮ ማረሚያ ቤት ቤት
- ምስራቅ ሸዋ (አዳማ) ማረሚያ ቤት
2. አጭር የቴክኒክ መግለጫ
- 500 ሊትር የመያዝ አቅም ያለው
- Stainless Steel (SS-304 ወይም ከዝገት-ነጻ ብረት ወይም ተመሳሳይ ቁስ)
- 7.5–10 HP, 380V / 50Hz, 3-Phase
- ተቀያያሪ የማቀላቀያ ፍጥነት (Mixing speed)- Variable /Adjustable Speed Control)
- Emergency Stop (የአስቸኳይ ጊዜ ማቆሚያ)
- የደህንነት (የመከላከያ) ሽፋን
- የማፍሰሻ ስርዓት-የታችኛው መፍሰሻ ቫልቭ
- ማሽኑን በቦታው የመትከል ፤ አጭር ስልጠና ለሰልጣኞች መስጠት እና የመጀመሪያ የምርት ሙከራ ማድረግ
- ቢያንስ 1 ዓመት ዋስትና መስጠት የሚችል
- ማሽኑ ከዚህ በፊት በጥቅም ላይ ያልዋለ
- የማሽን የመጠቀሚያ መመሪያ በአማርኛ ወይንም በእንግሊዝኛ (User Manual)
3. የተወዳዳሪዎች መስፈርት
ተወዳዳሪዎች፦
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የምዝገባ ሰርተፊኬት
- የVAT / TIN ምስክር ወረቀት
- ከላይ የተገለጹትን ማሽኖች የማምረት (ተመሳሳይ ሥራ ልምድ) ያለው
- ማሽኑን በተመለከተ ከሌሎች ድርጅቶች የተሰጡ ምስክርነቶችና ተያያዥ ዶክመንቶች
4. የጨረታ ሰነድ መላኪያ እና መክፈቻ
- ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣ ቀን ከየካቲት 1 ቀን 2018-የካቲት 10 ቀን 2018 ድረስ፤ ለአስር ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በማግስቱ ማለትም የካቲት 11 ቀን ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ ህጋዊ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ውክልና ያላቸው ተጫራቾች በሚገኙበት የጨረታው ሰነድ በቢሮአችን የሚከፈት ይሆናል።
- ጨረታው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይቀርባል
- ቴክኒካል እና ፋይናንሺአል ሰነዶች ለየብቻቸው ይቀርባ
- ጨረታው በተወሰነው ቀን በJFA-PFE ቢሮ ውስጥ ይከፈታል
5. አጠቃላይ ማስታወሻ
- JFA-PFE ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው
- ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታ ሰነድ የተገለፀውን መመሪያ መከተል አለበት
6. የድርጅቱ አድራሻ
ከቦሌ-ደንበል ሲቲ ሴንተር ወደ መስቀል ፍላወር በሚወስደው መንገድ ከጋዜቦ አደባባይ ዝቅ ብሎ አርሾ ሜዲካል ላቦራቶሬ አጠገብ ይገኛል።
ስልክ ቁጥር፡ +251 11 850 4400 ወይንም +251 91 113 4194
ፖ.ሳ.ቁ. 2366 Code 1110
Email: contact@jfapfe.org