የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበርያና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 09, 2026)

በድጋሚ የወጣ

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 006/18

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበርያና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በአውሮፓ ህብረት ያልተማከለ አደጋ ስጋት ቅነሳ ፕሮጀክት በተገኘ ድጋፍ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የዕቃው ዓይነት

ብዛት

1

Workstation Core i9 based on technical specification

1

2

Desktop Computer core i5 based on technical specification

7

3

Color printer based on technical specification

1

4

Scanner based on technical specification

1

5

UPS 1500 VA based on technical specification

3

 

  1. ተጫራቾች በግልጽ የሚነበብ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፊኬት፣ ኦንላይን የአቅራቢነት ምዝገባ እና ሌሎች አስፈላጊ ማስረጃዎቻቸውን በግልጽ እንዲነበብ አድርገው ማቅረብ አለባቸው።
  2. አስገዳጅ የሆኑ የዕቃዎች ቴክኒካል እና ሌሎች ዝርዝር መስፈርቶች ከመደበኛ የጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዞል።
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 02/06/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 13/06/2018 ዓ/ም ድረስ ከቢሮው ግዥና ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500.00 በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
  4. የጨረታ ማስከበሪያ 45,000 (አርባ አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት CPO ማቅረብ አለባቸው።
  5. የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ፋይናንሻል አንድ ዋና ኦርጅናል እና ተጨማሪ አንድ ኮፒ ጋር እንድሁም ቴክኒካል አንድ ዋና ኦርጅናል እና ከተጨማሪ አንድ ኮፒ ጋር በማዘጋጀትና በአንድ ፖስታ ዉስጥ በመክተት በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ10ኛው ቀን ከሰዓቱ 8፡00 ሰዓት ድረስ በሲዳማ ብሔራዊክልላዊ መንግስት ድጋፍ ማስተባበርያና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ግዥና ንብረት አስተዳደር ክፍል ለዚሁ አግልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት።
  6. የጨረታው ሣጥን በቀን 16/6/2018 ከሰዓቱ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድጋፍ ማስተባበርያና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ግዥና ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል ይሁንና የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም።
  7. የጨረታ ሳጥን ከሚታሸግበት ሰዓት በኋላ የመጣ ሰነድ ሳይከፈት ተመላሽ ይደረጋል።
  8. ተጫራቾች የገዙት የጨረታ መደበኛ ሰነድ ተፈርሞበትና የተጫራቾች ማኅተም ተደርጎበት ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ታሽጎ ይመለሳል። ነገርግን ይህ የጨረታ ስነድ ተፈርሞበትና ማኅተም ተደርጎበት ለገዢው መሥ/ቤት ካልተመለሰ ጨረታውን እንዳልተወዳደሩ ይቆጠራል።
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰብያ፦ የጨረታ ሳጥን መክፈቻ እና መዝጊያ ቀን የሥራ ቀን ባይሆን የጨረታው ሳጥን የማሸጉም ሆነ የመክፈቱም ሥነ-ሥርአት የሚከናወነው በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ  በተገለጸው ሰዓት እና ቦታ ይሆናል።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 212 4639 ይደውሉ

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበርያና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *