Your cart is currently empty!
የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Addis Zemen(Feb 09, 2026)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት አቶ ጋሻው ገረመው እና የፍ/ባለዕዳ እነ አቶ ሳሙኤል ገረመው መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/250205 በሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ/ም በተደረገው ስምምነት 250205 በ09/11/2016 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/261768 በ1/08/2017 ዓ/ም በዋለውችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የቤት ቁጥር 496 የይዞታ መለያ ኮድ AA000010701826 በእነ መሰረት አቦዬ በዳኔ ስም የተመዘገበ የይዞታው ስፋት 145 ካ/ሜ በከተማ ፕላን መሰረት የኮሪዶር ልማት ክልል ውስጥ በአብዛኛው የገባ ሲሆን የመሬት አጠቃቀም B-2 መካከለኛ ጥግግት ቅይጥ መኖርያ 60% ጠቅላላ የወለል ምጣኔ ለመኖርያ አገልግሎት የሚውል ሲሆን በምዕራብ በኩል ባለ 10 ሜትር መንገድ እንለው እና በመንገድ በኩል 13.58 ካ/ሜ እንደሚነካው በሰሜን በኩል የኮሪዶር የመንገድ ዲዛይኑ እንደሚያሳየው 20.19 ካ/ሜ እንደሚነካው የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 5,418,878 (አምስት ሚሊዮን አራት መቶ አስራ ስምንት ሺህ ስምንት መቶ ሰባ ስምንት ብር ብር) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መጋቢት 4 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት