Your cart is currently empty!
የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Addis Zemen(Feb 09, 2026)
በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ ባለሙበት አቶ ናትናኤል ታከለ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ወ/ሮ አንስተ በቀለ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/185278 በ7/7/2015 ዓ/ም በሰጠው ፍርድ እና በኮ/መ/ቁ/189853 በ16/8/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በሟች አቶ ታከለ ገብሬ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 5 የቤት ቁጥር 480 በካ/ቁ/18183/10769/01 ባለ ሁለት ፎቅ መኖርያ ቤት የይዞታው ስፋት 732 ካ/ሜ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 53,663,940 (ሃምሳ ሶስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ስልሳ ሶስት ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ ብር) ሆኖ ታህሳስ 17 ቀን 2016 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል የሚል ማስታወቂያ ወጥቶ በእለቱ ተጫራች አልቀረበም። ይህንኑ ለፍ/ቤቱ ሪፖርት ተደርጎ ፍ/ቤቱ በ30/4/2016 ዓ/ም አሁንም ፍ/ቤቱ በ19/05/2018 ዓ/ም በድጋሚ ጨረታ እንዲወጣ ትዕዛዝ የሰጠ በመሆኑ በሁለተኛ ጨረታ የሚያዘው 1/4ኛ ብር 13,415,985 (አስራ ሦስት ሚሊዮን አራት መቶ አስራ አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ አምስት ብር) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ በመጋቢት 4 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/ አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት