ሜልባ ፕሪንቲንግ፣ ፐብሊሺንግና ፓኬጂንግ ኢማ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለህትመት አገልግሎት የሚውል ውድፍሪ ወረቀት ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 11, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ ሜልባ////007/2018

ሜልባ ፕሪንቲንግ፣ ፐብሊሺንግና ፓኬጂንግ ኢማ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለህትመት አገልግሎት የሚውል ውድፍሪ ወረቀት ለመግዛት ይፈልጋል።

.

የእቃው ዓይነት

መለኪያ

ብዛት

የጨረታ ማስያዣ መጠን

የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት

የጨረታ ፈቻ ቀንና ሰዓት

1

Wood free paper 80 GCS 84CM

ቶን

450

የአጠቃላይ ኮንትራት ዋጋ1% ግን   500,000.00 ብር ያልበለጠ

19/06/2018 ከቀኑ 800

19/06/2018 ከቀኑ 8:10

 በዚህ መሰረት

  1. በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች አግባብነት ያለው 2018 የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት፤ በጨረታው መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም የአቅራቢዎች ምዝገባ (suppliers list) ላይ መመዝገባቸውን የሚገልጽ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00/ ሶስት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ዋና ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከድርጅቱ /ቤት የግዥ ዳይሬክቶሬት 2 ፎቅ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዋናውንና ቅጅ በተለያየ ፖስታ በማሸግና ሁሉንም በአንድ ላይ በሚይዝ በሰም በታሸገ ፖስታ ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ እስከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ድረስ በአክሲዮን ማህበሩ ዋና /ቤት 2 ህንጻ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በድርጅቱ ዋና /ቤት ይከፈታል፡፡
  6. አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ቦሌ ሚካኤስ ኢጃ ዲቬሎፐር ህንጻ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ አጠገብ

ለተጨማሪ ማብራሪያ .. +251 0118550083/+251911968780

ፊንፊኔ/ኢትዮጵያ

ሜልባ ፕሪንቲንግ ፐብሊሺንግና ፓኬጂንግ አ.ማ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *