Your cart is currently empty!
ሜልባ ፕሪንቲንግ፣ ፐብሊሺንግና ፓኬጂንግ አ.ማ. በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ የተለያዩ የማተሚያ ማሽን ወረቀቶች ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 11, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ ሜልባ / ብ/ ግ/ማ/ጫ/088/2018
ሜልባ ፕሪንቲንግ፣ ፐብሊሺንግና ፓኬጂንግ አ.ማ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ የተለያዩ የማተሚያ ማሽን ወረቀቶች ለመግዛት ይፈልጋል::
|
ተ.ቁ |
የእቃው ዓይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
የጨረታ ማስያዣ መጠን |
የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
Art Paper 250 GSM 61*86 CM |
ሪም |
10,000 |
የአጠቃላይ ኮንትራት ዋጋ 1% ግን ከ500,000.00 ብር ያልበለጠ
|
19/06/2018 ከቀኑ 9፡00 |
19/06/2018 ከቀኑ 9፡10
|
|
2 |
Woodfree 80 GSM 61*86 CM |
ሪም |
1,500 |
|||
|
3 |
Bristol Paper 180 GSM61*86 |
ሪም |
1,500
|
በዚህ መሰረት ፡–
- በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች አግባብነት ያለው የ2018 የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ስርተፊኬት፤ የግብር ከፋይሰርተፊኬት፤ በጨረታው መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም የአቅራቢዎች ምዝገባ (suppliers list) ላይ መመዝገባቸውን የሚገልጽ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00/ ሶስት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ዋና ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከድርጅቱ መ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 2ኛ ፎቅ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋርማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ9o ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዋናውንና ቅጅ በተለያየ ፖስታ በማሸግና ሁሉንም በአንድ ላይ በሚይዝ በሰም በታሸገ ፖስታ ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ እስከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ድረስ በአክሲዮን ማህበሩ ዋና መ/ቤት 2ኛ ህንጻ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡
- አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– ቦሌ ሚካኤስ ኢጃ ዲቬስፐር ህንጻ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ አጠገብ
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስ.ቁ.+251 0118550083-/ +251911968780
ፌንፊኔ/ኢትዮጵያ
ሜልባ ፕሪንቲንግ፣ ፐብሊሺንግና ፓኬጂንግ አ.ማ