Your cart is currently empty!
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ለደንብ ልብስ የሚውሉ መገልገያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 11, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ የግዥ መለያ ቁጥር 006/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ለደንብ ልብስ የሚውሉ መገልገያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ሎት አንድ – ዩኒፎርም (ለወንድ ሙሉ ልብስ ኮትና ሱሪ፣ ለሴት ኮትና ጉርድ ቀሚስ ወይም ኮትና ሱሪ ተሰፍቶ የተዘጋጀ ሸሚዝ፣ ከረቫት፣ የውስጥ ልብስ እና አጭር የቆዳ ጫማ ለወንድና ለሴት እንዲሁም ደረት ላይ የሚደረግ ተሰኪ ወይም ተንጠልጣይ ሎጎ)
በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ።
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የቴክኒክ ኘሮፖዛል “አንድ ኦርጅናል ኮፒ” እና የፋይናንሻል ዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር “አንድ ኦርጅናል ኮፒ የድርጅቱ ስም፣ አድራሻ እና ማህተም እንዲሁም የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት ሎት በመፃፍ እና በየሎቱ በመለየት በታሸገ ኤንቨሎኘ በማቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ እለት ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን (በሚቀጥለው የሥራ ቀን) ከቀኑ 4፡00 ሰዓት በግዥና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 202 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መክፈቻ ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ጠቅላላ ከሚወዳደሩበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ ለሎት አንድ 2%፣ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ CPO ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። C.RO መሥራት ያለበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በሚል አድራሻ መሆን አለበት።
5. ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ጨምሮ በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ሜክሲኮ አፍሪካ ኅብረት ፊት ለፊት አማጋ ሕንፃ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 205 ግዥ ይች አገልግሎት ቡድን በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተእታ ቫት/ ጨምሮ ወይም ተእታ ቫት/ በፊት መሆኑን መግለጽ ይጠበቅባቸዋል። ያልተገለፁ ከሆነ ተ.እ.ታ ቫት/ ጨምሮ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል።
7. ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀባቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ በአሸነፉበት ሎት ከጠቅላላ ዋጋው 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል።
8. ተጫራቾች በጨረታው ሰነዱ የተገለፀው የመጫረቻ ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ በኋላ ወይም በጨረታው ሰነዱ በተገለፀው የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ራሱን ከጨረታው ካገለለ እና የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውለታ ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል።
9. ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ሁሉም ደንብ ልብሶች ላይ የጨረታ ሰነዱን ከማስገባታቸው በፊት ናሙናዎችን ለግዥ አገልግሎት ቡድን ማስገባት አለባቸው።
10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፋባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መሥሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
11. ለጨረታ ከቀረቡት ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ እስከ 20% /ሃያ ፐርሰንት/ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ
- በስልክ ቁጥር 011 557 5742 /011 557 5719 በመደወል ወይንም ሜክሲኮ ከገነት ሆቴል ገባ ብሎ አፍሪካ ኅብረት ፊት ለፊት አማጋ ሕንፃ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 205 ግዥ አገልግሎት ቡድን በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።
የአዲስ አበባ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ