Your cart is currently empty!
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት የካሜራ ግዥ እና ኢንስታሌሽን እንዲሁም የካሜራ አክሰሰሪ ግዥ ለመፈፀም፤ በዘርፉ የተሰማሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 11, 2026)
ጨረታ ማስታቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት የካሜራ ግዥ እና ኢንስታሌሽን እንዲሁም የካሜራ አክሰሰሪ ግዥ ለመፈፀም፤ በዘርፉ የተሰማሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ሊያሟላ የሚችል መወዳደር ይችላሉ።
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ (ታክስ ክሊራንስ) ማቅረብ የሚችሉ ፣
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ እና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
4. የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
5.የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
6. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደደር ህንፃ) አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ተጫራቾች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10/ ለአስር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርበው ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት በመክፈል ሰነድ መግዛት እና ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ።
7 ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር ) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ ፒ ኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት።
8. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (ለአስር) ተከታታይ ቀናት በፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም ) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት በዕለቱ 4፡00 ሰዓት በሮ ቁጥር 54 ይከፈታል። ይህ ቀን የበዓል ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ቀን ይሆናል።
10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 046-212-1334
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ