Your cart is currently empty!
የሳሪስ ልማተ ገበያ አዲስ ህይወት አክሲዮን ማህበር በ4505 ካሬ ሜትር ላይ የተሰራ ባለ አምስት ፎቅ (G+5) ህንፃ ላይ የሚከናወኑ የተለያዩ የጥገና ስራዎችን የጥናት፣ የዲዛይን እና የጨረታ ሰነድ የሚያዘጋጅ እና የጥገና ስራውን በአማካሪነት የሚከታተል ብቁ ድርጅት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል
Reporter(Feb 11, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ (Invitation to Bid)
የጨረታ ቁጥር፦ 004/2018
የሳሪስ ልማተ ገበያ አዲስ ህይወት አክሲዮን ማህበር በ4505 ካሬ ሜትር ላይ የተሰራ ባለ አምስት ፎቅ (G+5) ህንፃ ላይ የሚከናወኑ የተለያዩ የጥገና ስራዎችን የጥናት፣ የዲዛይን እና የጨረታ ሰነድ የሚያዘጋጅ እና የጥገና ስራውን በአማካሪነት የሚከታተል ብቁ ድርጅት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
1. የአማካሪው ዋና ዋና የሥራ ድርሻዎች
- የህንፃውን ወቅታዊ ሁኔታ ዳሰሳ በማድረግ የጥገና ፍላጎቶችን መለየት።
- ለጣራ ወለል እና ለመጸዳጃ ቤቶች (Waterproofing)፣ ለክፍል ፓርቲሽን እና የሱቅ ሽንሸና ስራዎች፣ የውኃ ስርገት መከላከያ ለሴራሚክ ወለል ጥገና እና ለሌሎች ተያያዥ ስራዎች ዝርዝር የዕቃ ዓይነትና ብዛት እንዲሁም የዋጋ ማቅረቢያ እና የጥራት መገለጫ ማዘጋጀት።
- ጥገናውን የሚያከናውን ኮንትራክተር ለመምረጥ የሚያስችል የጨረታ ሰነድ ማዘጋጀት።
- የጥገና ስራው ሲጀመር የጥራት ቁጥጥር እና የሱፐርቪዥን ስራ መስራት።
2. ተጫራቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች
- ከደረጃ 4 በላይ
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ።
- ተመሳሳይ የህንፃ ጥገና በአማካሪነት ስራ ላይ ቢያንስ ለ5 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሥራ ልምድ ያላቸው፣
- በቂ ሙያተኛ የሰው ኃይል (Civil/Architect/Qty. Serveries) ያላቸው
- የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያለው
- ተጫራቹ ባለፉት 5 ዓመታት ውስጥ ያስመዘገበው አማካኝ ዓመታዊ የገንዘብ ዝውውር ቢያንስ ከ 2 ሚሊዮን ብር ወይም ከዚህ በላይ መሆን አለበት::
3. የጨረታ አቀራረብ
- ጨረታው አንድ ወጥ የሆኑ ዋና እና ቅጂ ሠነዶች መቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የቴክኒክ እና የዋጋ ሰነዶቻቸውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. የጨረታው መመዝገቢያ፣ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን
- የጨረታውን ሰነድ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዝርዝር የሥራ መመሪያ (ToR) እና ተያያዥ ሰነዶች ከቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 24/06/2018 ድረስ ለተከታታይ 21 ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል።
- ጨረታው 25/06/2018 ከሰዓት 8፡00 ተዘግቶ በእለቱ 9፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
5. ማሳሰቢያ
- የሳይት ጉብኝት ቀን በጨረታው ቆይታ ጊዜ ውስጥ በ16ኛው ቀን ሆኖ ሠዓቱ በድርጅቱ ጽ/ቤት በኩል ለሁሉም ተጫራቾች በስልክ የሚገለጽ ይሆናል ::
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው ለስልሳ ቀናት ዋጋው ጸንቶ ይቆያል::
አድራሻ፡– በአ/ቃሊቲ ክ/ከተማ ወ/06 ሳሪስ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባቡር ፌርማታ ፊት ለፊት ከሬዮስ ኢንጂነሪንግ አጠገብ የሚገኘው የሳሪስ ልማተ ገበያ ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502
ለተጨማሪ መረጃ፦ ስልክ ቁጥር 0114-42-21-21 ወይም 0910-87-00-41 ወይም 0948-21-22-21 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
የሳሪስ ልማተ ገበያ አዲስ ህይወት አክሲዮን ማህበር!!