Your cart is currently empty!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተደዳር ለተለያዩ የንግድ ስራዎች በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 15 ያስገነባቸውን ሁለገብ የገበያ ማዕከላት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የፅዳት ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 10, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
- የጨረታ ዓይነት
- የገበያ ማእከላት የፅዳት ስራ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተደዳር ለተለያዩ የንግድ ስራዎች በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 15 ያስገነባቸውን ሁለገብ የገበያ ማዕከላት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የፅዳት ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የመወዳደሪያ መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል ።
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
1. ከላይ ከተጠቀሰው ስራ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው የ2018 ዓ/ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ዋናውና ኮፒውን ማቅረብ የሚችል፣
2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ( Tin number) ያለው ዋናውንና ኮፒ ማቅረብ የሚችል፣
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (vat) ተመዝጋቢ የሆነ ዋናውንና ኮፒ ማቅረብ የሚችል
4. በገንዘብ ሚንስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር (supplies list) የተመዘገበ ሆኖ ከሚመለከተው አካል የተሰጠውን ማስረጃ ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ የሚችል፣
5. ከሚያገኘው ገቢ ላይ 3% ታክስ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ ፣
6. ማንኛውም ተጫራች ካቀረበው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 2% በንግድ ቢሮ ስም CPO(ጋራንትድ ቦንድ) እውቅና ካለው ባንከ የጨረታ ማስከበሪያ በማሰራት ማስያዝ የሚችል፤
7. ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ ከጠቅላላ ዋጋ ላይ እውቅና ካለው ባንክ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ የሚችል፤
8. ከሙስናና መሰል ብልሹ የአሰራር ተግባራት ነጻ የሆነ በፌዴራል እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጡ ህጎችን የሚያከብር፡
9. የድርጅቶችን እና ተቋማትን የጽዳት ስራዎችን የሚከናውኑበትን የአሰራር ስልት እና የሚመራበትን የሚገልጽ አጭር ሪፖርት ሰነድ ማቅረብ የሚችል፣
10. ድርጅቱ የሁለገብ ገበያ ማዕከሉን በአካል በማየት የጽዳት ስራው የሚያስፈልገውን የሰው ኃይልና ለአንድ ሰው የሚያስፈልገው የወር ክፍያ መጠን ፕሮፖዛል ሰነድ ማቅረብ ይኖርበታል።
11. የመልካም ስራ አፈጻጸም ምስክርነትን የሚገልጽ ማስረጃዎችን ዋናውን እና ኮፒ ማቅረብ የሚችል፤
12. በተጠቀሰው በዚህ ስራ በቀጥታ 3 አመት እና ከዚያ በላይ የስራ ልምድ ያለው እና ማስረጃዎችን ዋናውን እና ኮፒ ማቅረብ የሚችል
13. ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ 1000(አንድ ሺህ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከመስሪያ ቤቱ አድራሻ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ደጃች ውቤ 1888 ህንጻ 8ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 803 መግዛት ይችላሉ።
14. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጫራቹ ድርጅት ስልጣን ያለው አካል (የድርጅቱ ባለቤት ወይም ዋና ስራ አስኪያጅ) ስም፣ ፊርማ፣ የድርጅቱ ማህተም፣ እንዲሁም የድርጅቱ ሙሉ አድራሻ፡ ስልክ ቁጥር በፖስታው ላይ በመግለጽ፣
13.1 ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ
13.2 ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በማድረግ በሰም በታሸገ ፖስታ CPO ጨምሮ በተለያየ ፖስታ ለየብቻው ማቅረብ ይኖርባችኃል፣
15. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ንግድ ቢሮ የግዢ ዳይሬክቶሬት 8ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 803 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
16. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ16ኛው ቀን ይከፈታል ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ንግድ ቢሮ 9ኛ ፎቅ አዳራሽ ይከፈታል። ጨረታው በሚከፈትበት እለት ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባለመገኘታቸው ምክንያት ጨረታውን ከመከፈት አያስቀርም፡፡ ጨረታው የሚዘጋበትና ሚከፈትበት እንዲሁም የቢሮ ቁጥር ለውጥ ካለ በውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን፣
16. አሸናፊ የሆነ ተጫራች አሸናፊ መሆኑ በቢሮው ከተለጸለት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከንግድ ቢሮ ጋር ውል መፈጸም አለበት፡፡
17. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ ስ.ቁ..0111703024 በመደወል መረጃ መጠየቅ
ይቻላል።
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ደጃች ውቤ ወረዳ 5 1888 ህንጻ 8ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 803
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ