Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የምግብ ነክ ቁሳቁሶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Reporter(Feb 11, 2026)
የምግብ ነክ ቁሳቁሶች ግዥ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የምግብ ነክ ቁሳቁሶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
1. የታሸገ ውሃ 0.6 ሊትር
2. ዳይጄስቲቭ ብስኩት 220 ግራም
3. የህፃናት ወተት 400 ግራም
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
1. በዘርፉ የተሰማሩ የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ፣ የ2018 ዓ.ም የታደለ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ሰርተፍኬት፣ በጨረታው መሳተፍ የሚያስችል ከገቢዎች ክሊራንስ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. አንዱ ተጫራች በሌላዉ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት ከጨረታዉ የሚያሳግድ ይሆናል።
3. ተጫራቶች ከጨረታው በኃላ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድቦንድ ለሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ (2%) በCPO ወይም ባንክ ጋራንቲ አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር መሆኑን ወይም አለመሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራች ጨረታውን በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር (10) የስራ ቀናት ውስጥ ጨረታ ሰነዱን በጉርድ ሾላ ሳሊህተ ምህረት ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ድራር ሞል አጠገብ ከሚገኘው ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመገኘት የጨረታውን ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ስነድ በብር (800) ብር (ስምንት መቶ ብር) በመግዛት የጨረታ ሰነዳችሁን እስከ ማክሰኞ የካቲት 13/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
6. ተጫራች ጨረታውን አሸንፎ ባቀረበዉ ሰነድ መሰረት እቃዎቹን ሳያቀርብ ቢቀር ያስያዘው በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ድርጅቱ ገቢ ያደርጋል ወይም ተመላሽ አይሆንም።
7. ጨረታ ሰነዶችና ከጨረታው ጋር ተያያዥ የሆኑ ሰነዶች ማለትም ቴክኒካል ዋናውና ኮፒ እና ፋይናንሻል ዋናውና ኮፒ ዶክመንት በፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያው ሰዓት በፊት ለዚህ በተዘጋጃው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማሰገባት አለበት።
8. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ቁሳቁሶች የአገልግሎት ጊዜያቸው አንድ አመትና ከዚያ በላይ መሆን ያለበት ሲሆን ለዚህም ለሚያቀርቧቸው ቁሳቁሶች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
9. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ተጫራጮቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ሳይቀይሩ በትእዛዙ መጠን እስከ 25 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው።
10. ጨረታው የካቲት 13/2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 8፡30 በጉርድ ሾላ በሚገኘው ሳህሊተ ምህረት ቤተክርስያን ፊት ፊት ለፊት ድራር ሞል አጠገብ በሚገኘዉ የማህበሩ መሰብሰቢያ አደራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
11. አሸናፊው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተገለፀለት ወይም የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ የምግብ ቁሳቁሶችን ከ7 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ወይም በውሉ መሰረት ማቅረብ ይኖርበታል።
12. ተጫራቾች ያሸነፉትን ምግብ ነክ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን በድርጅቱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
13. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጫራቾች ስለጨረታዉ ተጨማሪ ማብራሪያ ሲፈልጉ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ስልክ በመደወል ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር፡ 011-515-0608
ፖስታ ሳጥን ቁጥር፡ 41076