Your cart is currently empty!
ዲኬቲ ኢትዮጵያ ለድርጅቱ የቢሮ አገልግሎት የሚዉሉ ሶስት (03) ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Reporter(Feb 11, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ዲኬቲ ኢትዮጵያ (ድንቅ ክስተት ለጤና) የተባለ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ማህበራዊ ግብይትን በመከተል የቤተሰብ እቅድን ለማስፋፋት፣ ኤችአይቪን ለመከላከል፣ እንዲሁም የእናቶችና ህፃናት ጤናን ለመጠበቅ የሚያስችሉ ምርቶችን በማሰራጨት በሲቪል ማህበረሰብ ባስስልጣን በምዝገባ ቁጥር 0062 ተመዝግቦ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በኤችአይቪ እና የስነ ተዋልዶ ጤና ላይ የራሱን አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ያለ የዉጭ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ለድርጅቱ የቢሮ አገልግሎት የሚዉሉ ሶስት (03) ተሸከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
1. ስለጨረታ የሚገልጸውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰአት ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምር በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
2. ተጫራቾች በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አስባቸው።
3. የመኪና ማስረከቢያ ቦታ ከገርጂ ወደ ጉርድ–ሾላ በሚወስደው መንገድ ከጉና መጋዘን ቀጥሎ በሚገኘዉ መጋቢ መንገድ ላይ ወጋገን ባንክ ገባ ብሎ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት
4. አሸናፊው ከታወቀ በኃላ በ10 ቀናት ውስጥ መኪናው ማስረከብ የሚችል
5. የጨረታ ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን የካቲት 11/2018 ከሰዓት 11:00
6. የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት: የካቲት 12/2018 ከሰዓት 8:00
7. የጨረታ መክፈቻ ቦታ: በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል። ሆኖም ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተባስ ቀንና ሰዓት ባይገኙም ጨረታዉ የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን።
8. ድርጅቱ ማንኛውንም ጨረታ በሙሉ ወይም በከፊል ያስምንም ግዴታ የመቀበል ወይም የመሰረዝ መብት አስሙ።
ስልክ ቁጥር +251911317100/ 251911357228