በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክ/መንግስት በቀቤና ልዩ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ተገጣጣሚ መቀመጫ ወንበር በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክ/መንግስት በቀቤና ልዩ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ተገጣጣሚ መቀመጫ ወንበር በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Jun 07, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 04

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክ/መንግስት በቀቤና ልዩ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለቀቤና ልዩ ወረዳ ም/ቤት ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ግልጋሎት የሚውል ተገጣጣሚ መቀመጫ ወንበር በዝቅተኛ ዋጋ ከሚያቀርቡ አቅራቢዎች 230 እስከ 250 የሚደርስ ወንበሮች ከመግጠሚያ ዋጋ ጋር በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ከዚህ በታች በቀረበው መስፈርት መሰረት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች

1. በፈርኒቸር ተገጣጣሚ የቢሮ እቃዎች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው

2. ቲን ነምበር ሰርተፍኬት ተመዝጋቢ የሆነ

3. የቫት ሰርተፍኬት ተመዝጋቢ የሆነ

4. ንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ተመዝጋቢ የሆነ

5. በአቅራቢነት የተመዘገበ ሰርተፍኬት የሚያቀርብ

6. የሚወዳደርበትን እቃ አይነት ናሙና ፎቶ ግራፍ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅበታል።

7. ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን፤ ጨረታው የሚታሸገው በ15 ቀን 6፡00ሰአት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 8፡00 ሰአት ላይ የሚከፈት ይሆናል። 15ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ የበአል ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የከፈታል።

8. የጨረታ ሰነድ ከግዥ ንብረት አስተዳደር ኬዝ-ቲም ክፍል ብር 300 ብር በመክፈል መወሰድ ይቻላል።

9. የጨረታው ማስከበሪያ በCPO/በሌላ የፋይናንስ አማራጭ ብር 50,000/ በቀቤና ልዩ ወረዳ ፋይናንስ ስም ማስያዝ ይጠበቃል።

10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ከገኘ በጨረታው አይገደድም።

ለበለጠ መረጃ
ስ.ቁ 011-330 1255/54 በመደወል ይጠይቁ።
ማ/ኢ/ከ/ወ/ቀ/ ል / ወ / ፋ / ጽ / ቤት
ወልቂጤ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *