Reporter (Jun 07, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ት/ት/ግዥ088/2018
ድርጅታችን ትራኮን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ልዩ ልዩ የአልሙኒየም ፕሮፋይሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
በዚሁ መሰረት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር ቀናት ውስጥ ዝርዝር የጫረታ ሰነዱን ከዋና ቢሮው ድረስ (ሰበታ) በመገኘት መውሰድ እና ዋጋ ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጫረታውን የሚሳተፉ ድርጅቶች የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል:: በዚሁ መሰረት የሚከተሉት ማሳሰቢያዎች ተግባራዊ ይሆናሉ::
- ድርጅቱ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉም ሆን በከፊል የመሰረዝ ወይም የማራዘም መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ድርጅቱ በጥቅል ዋጋም ሆነ በዝርዝር የፕሮፋይል ዋጋ ተመስርቶ አሸናፊውን የመለየት መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ድርጅቱ ለሽያጭ የቀረቡ ፕሮፋይሎችን ናሙና /ሳምፕል/ ተጫራቾች የጫረታ ሰነድ በሚወስዱበት ወቅት በአካል ቀርበው እንዲመለከቱ ያመቻቻል::
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ያሸነፈበትን ዋጋ ከፍሎ ፕሮፋይሎችን መረከብ ይችላል፡፡
- የባንክ ማረጋገጫ ሲያቀርብ ድርጅታችን ፕሮፋይሎችን ከገላን የድርጅቱ ንብረት ክፍል በራሱ (በተጫራቹ) ትራንስፖርት እንዲጭን ሁኔታዎችን ያመቻቻል::
- ተወዳዳሪዎች ለሚያስገቡት የጫረታ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 50,0000.00 (ሀምሳ ሺ ብር) ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የጫረታ ሰነዶቻቸዉን በታሸገ ፖስታ እስከ ሰኔ 6, 2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰአት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታዉ ሰኔ 6, 2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰአት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ጅሞ 3 አጫሉ መንገድ አካባቢ በሚገኘዉ ትራኮን ዋና መ/ቤት 4፡30 ይከፈታል::
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0911455448/0929918416/ +251 91 025 3030 ግዥ ክፍል መጠየቅ ይቻላል::
ትራኮን ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግል ማህበር