Reporter (Jun 07, 2026)
የሥራው ዝርዝር /ወሰን (Scope of Work)
ኢትዮ ሬይል ሎጅስቲክስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከ 5,000 (አምስት ሺህ) ቶን በላይ የሚመዝኑ፣ በካርቶን የታሸጉ ልዩ ልዩ እቃዎችን በብትን ጭነት (Break-bulk Cargo) መልክ ከጅቡቲ ወደብ ወደ አዲስ አበባ ለማጓጓዝ ይፈልጋል። በመሆኑም ብቃቱ ያላቸውን ድንበር ተሻጋሪ የትራንስፖርት ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
1.2 ህጋዊ መስፈርቶች እና የብቃት ማረጋገጫ (Eligibility Criteria)
ተጫራቾች ህጋዊነታቸውን የሚያረጋግጡ የሚከተሉትን ሰነዶች ኮፒ ከቴክኒክማቅረቢያው ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል። እነዚህን ሰነዶች ያላቀረበ ተጫራች ያለምንም ተጨማሪ ግምገማ ከጨረታው ውጪ ይሆናል፡፡
- በዘመኑ (በአሁኑ የበጀት ዓመት) የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፤
- በዘመኑ የታደሰ የድንበር ተሻጋሪ ደረጃ ፈቃድ ወይም የመንገድ ትራንስፖርት ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤
- ለጨረታው የሚሆን ወቅታዊ የግብር ክሊራንስ (Jax Clearance) ምስክር ወረቀት፤
1.3 የቴክኒክ አቅም መስፈርቶች (Technical Capacity)
የተሽከርካሪዎች ብዛትና አቅም፦ በአንድ ጊዜ/በአንድ ጥሪ ከ 50 (ሃምሳ) በላይ የሆኑና እያንዳንዳቸው 400 (አራት መቶ) ኩንታል ወይም 40 ቶን የመጫን አቅም ያላቸውን ተሽከርካሪዎች ማሰማራት የሚችል።
የድርጅቱ የስራ ልምድ፦ በድንበር ተሻጋሪ (ከጅቡቲ ኢትዮጵያ) የጭነት ትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ቢያንስ 5 (አምስት) ዓመት እና ከዚያ በላይ የሥራ ልምድ ያለው (ይህንን የሚገልጽ የማስረጃ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል)።
ክፍል 2፡ ለተጫራቾች የሚሰጥ መመሪያ (instructions to Bidders)
2.1 የጨረታ ዝግጅት ወጪ
ተጫራቹ ለጨረታው ሰነድ ዝግጅትና ለማስገባት የሚያወጣውን ማንኛውንም ወጪ ራሱ የሚሸፍን ሲሆን፣ ድርጅታችን ኢትዮ ሬይል ሎጅስቲክስ ለዚህ ወጪ ምንም ዓይነት ኃላፊነት አይወስድም።
2.2 ማብራሪያ ስለመጠየቅ
ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ግልጽ ያልሆነላቸው ወይም ማብራሪያ የሚያስፈልገው ነገር ካለ የጨረታው ማጠቃለያ ቀን ከመድረሱ በፊት ለድርጅቱ በጽሑፍ ወይም በኢሜይል ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
2.3 የጨረታ አቀራረብ ስነ–ስርዓት
ተጫራቾች የመወዳደሪያ ፖስታቸውን በሁለት (2) የተለዩ ኤንቨሎፖች በጥንቃቄ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፦
ፖስታ 1 (የቴክኒክ መወዳደሪያ)፦ ህጋዊ ፈቃዶች፣ የብቃት ማረጋገጫዎች፣ የ5 ዓመት የስራ ልምድ ማስረጃ እና የተሽከርካሪዎች ባለቤትነት ወይም ውል ማረጋገጫ የሚገኝበት።
ፖስታ 2 (የፋይናንስ መወዳደሪያ)፦ የአገልግሎት ዋጋ ዝርዝር (ከጅቡቲ አዲስ አበባ በቶን ወይም በኩንታል የሚጠየቀውን ዋጋ ታክስን ጨምሮ) የሚገልጽ።
2.4 የጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ
የቀረቡት የዋጋ ማቅረቢያዎች ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ ለ 90 ቀናት ጸንተው መቆየት አለባቸው።
ክፍል 3፡ የቴክኒክ ዝርዝር መግለጫ እና የሥራ ውል (Technical Specifications) የሥራው ዝርዝር መገለጫ / መስፈርት
የእቃው ዓይነት ፡ በካርቶን የታሸጉ ልዩ ልዩ ዕቃዎች (የብትን ጭነት) አጠቃላይ ክብደት ከ 5,000 (አምስት ሺህ) ቶን በላይ
የጉዞ መስመር፡ ከጅቡቲ ወደብ (Port of Djibouti) እስከ አዲስ አበባ
ዝቅተኛ የተሽከርካሪ ስምሪት፡ በአንድ ጊዜ 50 እና ከዚያ በላይ መኪናዎች
የአንድ መኪና አቅም፡ 400 ኩንታል (40 ቶን) እና ከዚያ በላይ
ደህንነትና ጥበቃ ፡– ጭነቱ በካርቶን የታሸገ በመሆኑ ተሽከርካሪዎች ከዝናብ፣ ከእርጥበትና ከስርቆት የሚከላከሉ ጥራት ያላቸው ሸራዎች (Jarpaulins) እና ገመዶች ሊኖሯቸው ይገባል፡፡
ክፍል 4፡ ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ጊዜ
4.1 የሰነድ ማስገቢያ ማጠቃለያ
ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱ መግባት አለበት:: ከቀጠሮው ሰዓትና ቀን ዘግይቶ የመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::
4.2 የመረከቢያ አድራሻ
ድርጅት፡ ኢትዮ ሬይል ሎጅስቲክስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
የቢሮ አድራሻ፡ አድራሻ አዲስ አበባ፤ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ 10፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ የቢሮ ቁጥር 05
ከተማ/አገር፡ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ስልክ ቁጥር፡ +25111 439 7665/ +251-911424084
ኢሜይል፡ WWW.ethiorail.com
4.3. ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ቀን እና ሰዓት
ጨረታው የሚዘጋበት ቀን እና ሰዓት፡– ሰኔ 07/2018 ቀን 4:00 ሰዓት
የሚከፈትበት ቀን እና ሰዓት ፦ሰኔ 07/2018 ቀን 4፡30 ሰዓት
ክፍል 5፡ የጨረታ ቅጾች (Tender Forms) – በተጫራቾች የሚሞላ
(በትራንስፖርት ድርጅቱ የሚሞላ)
የድርጅቱ ስም፦
በድንበር ተሻጋሪነት የቆየበት ዘመን፦ ዓመታት (የማስረጃ ደብዳቤ ይያያዝ)
ድርጅቱ በአጠቃላይ ያለው የ400 ኩንታል መኪናዎች ብዛት፦ ፍሬ ቅጽ 5.1፡ የተጫራቹ መገለጫ እና የተሽከርካሪ አቅም ማረጋገጫ በአንድ ጊዜ 50+ መኪናዎችን የማሰማራት አቅም አለዎት? [ ] አለኝ [ ] የለኝም
ቅጽ 5.2፡ የፋይናንስ (የዋጋ) ማቅረቢያ ቅጽ
(ይህ ቅጽ ተሞልቶ በፋይናንስ ፖስታ ውስጥ ብቻ መታሸግ አለበት) የአገልግሎቱ ዓይነት የመለኪያ አሃድ የአንዱ ዋጋ (በብር) ተጨማሪ ማብራሪያ (ቫትን ጨምሮ/ሳይጨምር)
የጭነት ማጓጓዣ ዋጋ (ከጅቡቲ ወደብ እስከ አዲስ አበባ) በኩንታል/ በቶን
ክፍል 6፡ አጠቃላይ የውል ስምምነት ሁኔታዎች (General Conditions of Contract)
(ጨረታውን አሽንፎ ውል ሲፈረም የሚተገበሩ ዋና ዋና ነጥቦች)
የውል ማስከበሪያ (Performance Security)፡- አሸናፊው ድርጅት ውል ከመፈረሙ በፊት የጠቅላላው ውል 10% የሚሆን የውል ማስከበሪያ ዋስትና (CPO ወይም የባንክ ጋራንቲ) ማቅረብ ይኖርበታል::
የዕቃ መጎደልና መበላሸት ኃላፊነት፦ እቃው በካርቶን የታሸገ በመሆኑ በጉዞ ላይ በሚደርስ የውሃ መግባት (የመበስበስ)፣ የመቀደድ ወይም የቁጥር መጎደል አደጋዎች ላይ የትራንስፖርት ድርጅቱ ሙሉ በሙሉ በካሽ የመተካት ኃላፊነት አለበት::