Reporter (Jun 07, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፡ YMFI/ግጭ003/18
የኛ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ በ2018/19 በጀት አመት የተለያዩ የቢሮ ኮምዊዉተሮች እና አክሰሰሪስ፣ የስቴሽነሪ፣ የጽዳት እቃዎች እቃዎች እና የስራ መሣሪያዎች እና ዕቃዎች (Tools and Equipment’s) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1ኛ. ሎት 1: የቢሮ ኮምዊዉተሮች እና አክሰሰሪስ
2ኛ. ሎት 2: –የስቴሽነሪ እቃዎች
3ኛ. ሎት 3: –የጽዳት እቃዎች
4ኛ. ሎት 4: –የስራ መሣሪያዎች እና ዕቃዎች
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይቻላል።
- ተጫራቾች በዘርፉ አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ቀበና አደባባይ ወደቤላ በሚወስደው መንገድ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንጻ ላይ በሚገኘው ግራውንድ ፍሎር ቢሮ ቁጥር 003 መውሰድ ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳዳቸዉ ከሎት 1 እስከ ሎት 5 የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ 50,000(ሃምሳ ብር) ብር ሲፒኦ (CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/Bid Bond/ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ90 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከላይ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ እስከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ግራውንድ ፍሎር ቢሮ ቁጥር 003 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላል።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 ተዘግቶ 8:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 107 አሸናፊዉ ይታወቃል።
የኛ ማይክሮፋይናንስ አክስዮን ማህበር
አድራሻ ፡ ቀበና አደባባይ ወደቤላ በሚወስደው መንገድ የፊዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
ህንጻ ግራውንድ ፍሎር ቢሮ ቁጥር 003 ስልክ፡ 0968 51 11 11/0913377777