ደራሽ ለመርካቶ ኃላ/የተ/ሁ/ ሸ/ህ/ስ/ማህበር ከሚያስተዳድራቸው ቤቶች ውስጥ የተለያዩ ቦታ የሚገኙ 2 ቤቶችን ለሙስሊም ስጋ ቤት አገልግሎት ብቻ ማከራየት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ደራሽ ለመርካቶ ኃላ/የተ/ሁ/ ሸ/ህ/ስ/ማህበር ከሚያስተዳድራቸው ቤቶች ውስጥ የተለያዩ ቦታ የሚገኙ 2 ቤቶችን ለሙስሊም ስጋ ቤት አገልግሎት ብቻ ማከራየት ይፈልጋል


Addis Lessan (Jun 06, 2026)

የሙስሊም ስጋ ቤት ኪራይ ጨረታ

ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደተሞከረው ማህበራችን ደራሽ ለመርካቶ ኃላ/የተ/ሁ/ ሸ/ህ/ስ/ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ክልል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በስሩ ከሚያስተዳድራቸው ቤቶች ውስጥ የተለያዩ ቦታ የሚገኙ 2 ቤቶችን ለሙስሊም ስጋ ቤት አገልግሎት ብቻ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ማንኛውም ቤቱን ተከራይቶ ለህብረተሰቡ አንድ ኪሎ በ520 ብር ለመሸጥ የሚስማማ ተከራይ ብቻ በጨረታው መሳተፍ የሚችል ሲሆን ቤቶቹም

1.በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 8 የቀድሞ ቀበሌ 10 ሻወል ደማ ት/ቤት አካባቢ የሚገኝ

2.በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 8 የቀድሞ ቀበሌ 06 ውስጥ የሚገኝ መሆኑን አውቃችሁ ከላይ በተዘረዘረው መሰረት ለመስራት የሚስማማ ተጫራች የማህበሩ ዋና ጽ/ቤት ለመገኘት እና ቤቶችን በአካል በመገኘት በመመልከት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 በመክፈል በመግዛት የሚከራዩበትን ዋጋ በመጥቀስ በስም በታሸገ ኢቨሎፕ በማድረግ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ላይ በማስገባት  መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- ማህበሩ በጨረታው የተሻለ ዘዴ ከአገኘ በጨረታው አይገደድም

አድራሻ፡- በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 8 የቀድሞ ቀበሌ 04 ከአውቶቡስ ተራ ወደ 7ኛ በሚወስደው መንገድ አጋማሽ ላይ የማህበሩ ዋና ጽ/ቤት ይገኛል፡፡
ስልክ ቁጥር 0112 73-35-91

ደራሸ ለመርካቶ ኃላ/የተ/ሁ/ ሸ/ህ/ስ/ማህበር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *