Be'kur (Jun 08, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒዬን ኃ.የተ የ2017/2018 ምርት ዘመን
- ሎት 1. 10,000 ኩ/ል ነጭ በቆሎ፣
- ሎት 2. 5,000 ኩ/ል ነጭ በቆሎ እንዲሁም
- ሎት 3. 5,000 ኩ/ል ስንዴ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸውና እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
2. የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማያያዝ አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ሰነዱን ከዩኒየኑ ግዥና ፋይናንስ ዲቪጂን በመውሰድና ዋጋ ሞልተው በማሸግ ፖስታው ላይ ሶስት ቦታ ማህተም በማድረግ ማስገባት አለባቸው፡፡
4. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ11 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ድረስ መግዛትና ማስገባት አለባቸው፤ በ11ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ የመክፈቻ ቀኑ በእለቱ በ11ኛው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
5. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጎልም፡፡
6. ተጫራቾች በኢትዮጲያ ብሄራዊ ባንክ በተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የክፍያ ትዕዛዝ የሚሰጥ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ የጠቅላላ ዋጋውን 2 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
7. የንግድ ፈቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን አለበት እዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
8. አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታተይ የሥራ ቀናት ውስጥ በኢትዮጲያ ብሄራዊ ባንክ በተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የክፍያ ትዕዛዝ የሚሰጥ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ የተወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ ማስገባትና ውል መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህንን ካላደረጉ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ብር ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
9. የማንሻ ቦታ ቡሬ ከተማ 04 ቀበሌ የሚገኘው መጋዝን ሲሆን የመጫኛና ልዩ ልዩ ወጭዎችን በገዥ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
10. በጨረታ ሰነዱ ላይ ያልተገለጹ ነገሮች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥ እና ሽያጭ መመሪያ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
11. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12. ማንኛውም ተጫራች የመንገድ እና የቀረጥ ወጭዎችን መሸፈን የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
13. የጨረታው መክፈቻ ቀን በአል ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀንና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
14. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 774 06 40 /10 32 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡
የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒዬን ኃ.የተ