Be'kur (Jun 08, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የባሕር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለ2018 በጀት ዓመት ለሰራተኞች አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 1. የደንብ አልባሳት (ብትን ጨርቅ)፣
- ሎት 2. የጽዳት እቃዎች፣
- ሎት 3. የደንብ አልባሳት (የተዘጋጁ ልብሶች) እንዲሁም
- ሎት 4. የደንብ አልባሳት (ጫማ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከህጋዊ ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ (የታደሰ) የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት ቴክኒካል ሰነዱን፣ ፋይናሻል ሰነዱን እና ሲፒኦ ኦርጅናል እና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ በዋናው ድርጅት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ ብቻ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /unConditional Bank Garanty/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ ቢሮ ቁጥር 202 ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ
በሚቀጥለው የስራ ቀን በ8፡30 ይከፈታል፡፡ - አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው ከተለየበት ቀን ጀምሮ ከ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ከድርጅቱ በመቅረብ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ እና ውል በመፈፀም የደንብ አልባሳቱን ባ/ዳር ከተማ ውሃ ድርጅት ንብረት ክፍል ድረስ በማቅረብ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 320 5079 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የባሕር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
ባሕር ዳር