Be'kur (Jun 08, 2026)
የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ/ከሳሽ ሽታሁን መኮነን እና በአፈ/ተከሳሾች ጌትነት ዳኛው መካከል ባለዉ የገንዘብ ክርክር ጉዳይ በአፈ ተከሳሽ አቶ ጌትነት ዳኛው ስም በአገው ግምጃ ቤት በእንጅባራ ከተማ 02 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ፣ በምዕራብና በደቡብ መንገድ እንዲሁም በሰሜን ክፍት ቦታ ተዋስኖ የሚገኘው ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 4,439,681.60 (አራት ሚሊዮን አራት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ሰማንያ አንድ ብር ከስልሳ ሳንቲም) በጫረታ ይሸጣል፡፡ ጨረታው ከሰኔ 01/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሀምሌ 01/2018 ዓ.ም ድረስ በተከታታይ 30 ቀናት ቆይቶ ሀምሌ 01/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 5፡30 እንዲሸጥ ሲል ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ወደ ጨረታው ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼ ኛውን በሲፒኦ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት